Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኮንትሮባንድ ንግድ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ መጨመሩን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን አስታወቀ

1 2,513

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኮንትሮባንድ ንግድ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉሙሩክ ባለስልጣን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ በጅግጅጋ ከተማ በፓናል ውይይት በተከበረው 10ኛው ሀገር አቀፍ የግብር እና ቀረጥ ሳምንት ላይ ነይ ይህን ያስታወቀው።

እንደ ባለስልጣኑ ገለጻ የኮንትሮባንድ ንግድ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን ለአምስት ዓመታት በተደረገው ጥናት ላይ ተመርኩዞ ነው ይፋ የተደረገው።

ባለፉት ስድስ ወራት እንኳ ከ400 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት በኮንትሮባንድ መልክ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉንም በማሳያነት አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ከበደ ጫኔ፥ የወጪ እና ገቢ ኮንትሮባንድ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና ማህበራዊ ዘርፎች ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ነው ብለዋል።

በተለይም የሰዎች ጤና ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ መድሃኒቶች ከውጭ ሀገራት ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ በመሆኑን በመግለጽ ይህም በጤና ላይ ጉዳት እያስከተለ ነው ብለዋል።

በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የኮንትሮባንድ ንግድን በመከላከል ረገድ ሊረባረብ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

በቀጣይም የኮንትሮባንድ ግንድ ለማስቆም እና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም የጠረፍ ንድን ህጋዊ ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ እንዲዘጋጅ እንደሚሰራም አቶ ከበደ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሃመድ፥ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል የክልሉ ህዝብ በንቅናቄ እየተሳፈተ ነው ብለዋል።

በቀጣይም ይህንን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ተናግረዋል።

የጅግጅጋ ከተማ እና የአካባቢዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው፥ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል እንሰራለን ብለዋል።

  1. Mulugeta Andargie says

    Guys!!! Shabia has well trained camel. The camels have abilities to go back to their places where they were loaded. As soon as the unknown activies are occurred, the caravan split and galloping as if they have facing danger, to the place where they start the trip. The person who is also know where they go and where they meet.

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy