Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ጉዳት ለደረሰባቸው ፋብሪካዎች ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደርጓል

0 349

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው ሁከትና ግርግር ጉዳት ለደረሰባቸው ፋብሪካዎች መንግስት ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለጸ።

ኮሚሽነሩ አቶ ፍጹም አረጋ እንደገለጹት፥ ጉዳት የደረሰባቸው የኢንቨስትመንት ተቋማት በፍጥነት አገግመው ወደ ስራ እንዲመለሱ የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል።

ባለሃብቶች ከውጭ የሚያስገቧቸው ዕቃዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲስተናገዱ ማድረግ፣ ባለሃብቶቹን ማወያየት፣ በቀጣይ ችግሮች እንደማይገጥማቸው ማሳመንና የገንዘብ ድጋፍ ይጠቀሳሉ።

በተደረገላቸው ድጋፍ መሠረትም በአማራ ክልል ባህርዳር ዙሪያ ያሉ የአበበ እርሻ ልማቶችና በኦሮሚያ ክልል ሰበታ አካባቢ ያሉ የኢንቨስትመንት ተቋማት ከጥቂቶቹ በስተቀር ወደ ስራ መመለሳቸውን ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ እንዳሉት በባህር ዳር ዙሪያ በአበባ ልማት ዘርፍ እንዲሁም በሰበታ አካባቢ በሆርቲካልቸራል፣ በማምረቻና ሌሎችም ዘርፎች የተሰማሩ ተቋማት በተደረገላቸው ድጋፍ ወደ ስራ የሚመለሱበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ከፍ ያለ ጉዳት ያጋጠማቸው በመሆኑ ወደ ስራ የመመለሻ ጊዜያቸው መራዘሙንም ተናግረዋል።

ተቋማቱ ከፈጠሩት የስራ ዕድልና ለሃገር ዕድገት ካላቸው ፋይዳ አንጻር፥ መንግስት ቅድመ ሁኔታ ሳያስቀምጥ እስካሁን 100 ሚሊየን ብር በመደገፍ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ አድርጓልም ነው ያሉት።

ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪም ባለሃብቶቹ በየዕለቱ የሚገጥማቸውን የኤሌትሪክ፣ የውኃና ሌሎች መሠረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት የቅርብ ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንም ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት።

በአሁኑ ወቅት ችግሩን አስመልክቶ ጥናቶች እየተካሄዱ መሆኑን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፥ የገንዘብ ድጋፉን ጨምሮ ሌሎች እገዛዎች ቀጣይ መሆናቸውንም አስረድተዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy