Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

121ኛ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ዝግጅት መጠናቀቁን የባህልና ቱሪዝም ሚ/ር ገለፀ

0 1,777

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

121ኛ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ዝግጅት መጠናቀቁን የባህልና ቱሪዝም ሚ/ር ገለፀ

የካቲት 17፣ 2009

የፊታችን የካቲት 23 ለ121ኛ ጊዜ በመላ ሀገሪቱ የሚከበረው የአድዋ የድል በዓል አከባበር ዝግጅት መጠናቀቁን የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር አስታወቀ፡፡

በዓሉ በዋናነት የታሪክ በተከወነበት አድዋ ከተማ ላይ በተለያዩ ዝግጅት በድምቀት እንደሚከበር በሚንስቴሩ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዘሃኝ አባተ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

በዓሉ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት፣  የአፍሪካ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች የውጭ ሀገር ቱሪስቶችና የሀገሪቱ ዜጎች በበዓሉ ላይ ይታደማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል፡፡

ከየካቲት 23 በፊትም በዓሉን አስመልክቶ በአዲስ አበባ የጥያቂና መልስ ውድድር፣ በብሔራዊ ሙዚየም የስዕል አውደ-ርዕይ፣ በብሔራዊ ትያትር የሙዚቃ ዝግጅት እና በኦሮሚያ ባህል ማዕከል የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡

በዓሉን ለመዘከር በየዓመቱ የእግር ጉዞ የሚያደረጉ ሰዎች በቀኑ አደዋ ከተማ ይደርሳሉ፤ በመዲናዋም የአደባባይ ትርኢትን ጨምሮ ሌሎች ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ ተመልክቷል፡፡

በዓሉ ህዝቡ በልማቱ የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ፋይዳው የጎላ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy