Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሃብትን የምታገኘው ከምትሞትበት አልጋ ላይ ነው Steve Jobs

0 793

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

“ሃብትን የምታገኘው ከምትሞትበት አልጋ ላይ ነው” (Steve Jobs)የአፕል ካምፓኒ መስራች ስቲቭ ጆብስ(አሁን በሂወት የለም) በካንሰር ህመም ምክኒያት ድርጅቱን ሲለቅ የድርጅቱ ጠቅላላ ሃብት ሰባት መቶ ቢሊየን ዶላር ነበር።ይህም ካምፓኒውን በአለም ታሪክ እጅግ ውዱ እንዲሆን አስችሎታል።ስቲቭ ከመሞቱ ከጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ እንዲህ የሚል ነገር ፅፎ ነበር። እስኪ እናብበው”እኔ በንግድ ህይወቴ ከስኬት የመጨረሻው ማማ ላይ ደርሻለሁ። በሌሎች ሰዎች አይንም በውጤታማነቴ ወደር የሌለኝ ምሳሌ ነኝ። ነገር ግን እኔ ከስራ ውጭ ለሌሎች ነገሮች ምንም ጊዜ አልነበረኝም። የህይወት ግቤ ባለፀጋ መሆን ብቻ ነበር።አሁን በዚህ ሰዓት ታምሜ አልጋ ላይ ስወድቅ ያሳለፍኩትን ጊዜ ማስታወስ ጀመርኩ። በመጨረሻም የተገነዘብኩት ያካበትኩት ሃፍትና ያገኘሁት እውቅና ከሞት ፊት ለ ፊት ስቆም ደብዛዛና ትርጉም የሌለው ነገር ነበር።በጭለማ ክፍል ውስጥ ቁጭ እንዳልኩ ለመተንፈስ የሚረዳኝን ማሽን ነቀልኩት። በቀስታ የሚያንጎራጉር ድምፅ ይሰማኛል። የፈጣሪየን እስትንፋስም ሰማሁ። ሞትም ሊወስደኝ በጣም ተቃርቧል።አሁን የተረዳሁት ነገር እስከ ህይወታችን ፍፃሜ ሃፍት ለማጋበስ ብቻ መሮጥ እርባና ቢስ እንደሆነ ነው። ሌሎች የምንሰራቸው ብዙ ነገሮች ስላሉ። ምናልባት የጓደኝነት ሂወት፣ የጥበብ ዝንባሌ፣ ልጅ እያለን ለማሳካት እናልመው የነበረ ነገር……ብዙ ብዙ።የማያቋርጥ የገንዘብ ፍለጋ የመጨረሻ ውጤቱ ልክ እንደኔ ውስብስብ ሰው መሆን ነው።በዘመኔ ያከማቸሁትን ሃፍት ከእኔ ጋር ይዥው ልሄድ አልቻልኩም።ከእኔ ጋር አብሮኝ ያለው በልቤ የቀረው የፍቅር ትዝታየ ብቻ ነው።እውነተኛ ተከታይህ፣ አጃቢህ፣ ጥንካሬን የሚሰጥህ፣ ለመንገድህም መብራት የሚሆንህ በልብህ ውስጥ ያከማቸኸው ፍቅር ብቻ ነው።በአለም ውስጥ በጣም ውዱ አልጋ በሽታህን የሚታመምልህ አልጋ ነው።አንድን ሹፌር መኪናህን እንዲነዳልህ፣ ሰርቶ ገንዘብ እንዲያመጣልህ ልትቀጥረው ትችላለህ። ነገር ግን ያንተን ህመም እንዲታመምልህ ወይም እንዲሸከምልህ ማድረግ አይቻልህም።ቁሳቁስ ነገር ቢጠፋህ ፈልገህ ማግኘት ወይ ደግሞ መግዛት ትችላለህ። አንዴ ከጠፋህ የማታገኘው ነገር ግን የህይወትክን ነው።አንድ ሰው ወደ ቤተ መፅሃፍት ቤት ሲሄድ አንድ ነገር ሊያስታውስ ይችላል። እሱም ምንድን ነው “የጤናማ ህይወት አኗኗር” የሚለውን መፅሃፍ ለማንበብ ጀምሮት ነገር ግን እንዳልጨረሰው ነው።በየትኛውም የኑሮ ደረጃ ሁን፣ በየትኛውም ሰዓት ሞት ከፊትህ እንዳለ አትዘንጋ።ለቤተሰቦችህ ዋጋ ያለው ፍቅር ይኑርህ። ለትዳር አጋርህ ዋጋ ያለው ፍቅር ይኑርህ። ለጓደኞችህ ዋጋ ያለው ፍቅር ይኑርህ።እራስክን በአግባቡ ተንከባከብ። ሌሎችንም እንደዛው።”ምንጭ፦ noble mind (ተርጓሚ፦ አክሊ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy