Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ህዝቡን የሚጠቅም አስተሳሰብ በመያዝ ለስኬታማ ስራዎች መረባበረብ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

0 318

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ስራ አስፈፃሚ የ6 ወራት የስራ አፋፃፀም ግምገማ በባህርዳር ዛሬ ተጀምሯል፡፡በስራአስፈፃሚው ውይይት ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤትና የብአዴንና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ጓድ አለምነው መኮነን እንደተናገሩት የሊጉ አመራሮች ህዝብን የሚጠቅም አስተሳሰብ በመያዝ ተጨባጭ ውጤተማ ተግባር ማምጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል የተቀደሰ ሀሳብ ጥንትም ነበረ ያሉት ጓድ አለምነው ችግሩ የሚስተዋለው የተቀደሰውን ሀሳብ ወደ ተግባር በመዋል በኩል ያሉ ችግሮች ናቸው ብለዋል፡፡የሊጉ ስራ አስፈፃሚ እየሄደበት ያለውን እንቅስቃሴ ያደነቁት ጓድ አለምነው አመራሩ የጀመረውን የአቅም ግንባታ ስራ በማጠናከር የወጣቱን ተጠቃሚነት እና ተሳትፎ እንዲጎለብት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ጓድ አለምነው በንግግራቸው በአፅንኦት እንዳስቀመጡት ‹‹ያለልፋት ውጤት የለም ያለልፋት ትርፍ ነገር የለም ስለሆነም በለስላሳ ጉዞ ውጤት አትጠብቁ ህዝብ የሚጠቅም አስተሳሰብ ከተግባራዊ እንቅስቃሴ ጋር ይዛችሁ ርብርብ አድርጉ ከሂደቱም ከውጤቱም ለመርካት መስዋትነትን ለመክፈል ተዘጋጁ›› በሚል ለሊጉ ስራ አስፈፃሚዎች መልእክት በማስተላለፍ ውይይቱ ውጤታማ እንዲሆን ተመኝተው ቆይታቸው የተሳካ እንዲሆን ያላቸውን ምኞት ገልፀዋል፡፡የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ስራአስፈፃሚ የ6ወራቱን የሊጉን ዝርዝር አፈፃፀም በመገምገም እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy