Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

መንግስት ከ2010 – 2014 የሚተገበር የማይክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ በስራ ላይ እንዲውል ወሰነ

0 512

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

መንግስት ከ2010 – 2014 የሚተገበር የማይክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ በስራ ላይ እንዲውል ወሰነ፡፡

 

የሚንስትሮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 24ኛ መደበኛ ስብሰባው በሁለት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ም/ቤቱ በመካከለኛ ዘመን የ2010 – 2014 የማይክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ላይ ወይይት በማድረግ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

የመካከለኛ ዘመን የማይክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ የመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂን በአግባቡ ተግባራዊ ለማድረግ ከበጀት ጋር ማስተሳሰር፣ ለልማቱ የሚያስፈልገውን የፋይናንስ ሃብት በተጨባጭ በመተንበይ የ2010 የፌደራል መንግስት የወጪ በጀት ጣሪያን መወሰን እንዲሁም በጀት በመካከለኛ ዘመን እይታ እንዲመራ የማድረግ ዓላማ አለው፡፡

ማዕቀፋ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የትግበራ ዓመታት ከተቀመጡ ግቦችና የትኩረት አቅጣጫዎች ጋር ተጣጥሞ የቀረበ ነው ተብሏል፡፡

ለ2010 በጀት አመት ዝርዝር በጀት ዝግጅት ማዕቀፍ ሆኖ እንዲያገለግል እና በሀገሪቱ የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት በሚደግፍ መልኩ ማዕቀፉ መዘጋጀቱንም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፅ/ቤት ለኢቢሲ  በላከው መግለጫ አመልክቷል ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ም/ቤቱ ሰርከም ሚኒራልስ ፖታሽ ሊሚትድ ኩባንያ ጋር የተደረገው የከፍተኛ ደረጃ የፖታሽ ማዕድን ማምረት ፈቃድ ስምምነት ላይ ተወያቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ይህም ስምምነት በዘርፉ ኢንቨስትመንትን ከማስፋፋት አንጻር ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ በመሆኑ በሥራ ላይ እንዲውል ምክር ቤቱ ወስኗል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy