Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ማሰልጠኛ ተቋሙን በኔልሰን ማንዴላ ስም ለመሰየም አቅድ መያዙ ተዘገበ

0 480

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የፌደራል ፖሊስን መደበኛና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከልን በዕውቁ የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ(ማዲባ) ስም ለመሰየም ዕቅድ መያዙን አይ ኦ ኤል ድረ-ገፅ ዘግበ።እኤአ በ1961 ኔልሰን ማንዴላ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱበት ይኸው ተቋም አሁን የፖሊስ ኦፊሰሮች ስልጠና እየተሰጠበት እንደሚገኝ በዘገባው ተመልክቷል።

የማዕከሉ ኮማንደር አለሙ ገብረየስ እንዳሉት የነፃነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ በማዕከሉ ለሶስት ወራት ስልጠና የወሰዱ ሲሆን ከከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች ጋርም የምስጢር ስብሰባ ያከናውኑበት ነበር። በተጨማሪም ማንዴላ የተኩስና ሌሎች ልምምዶችንም ያደርጉ እንደነበር ኮማንደሩ ተናግረዋል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኦፊሰር አቶ ዳንኤል ምክረ በበኩላቸው መንግስት ጉዳዩን ለማሳወቅ እንዳልዘገየ በመጠቆም ታጋዩ በዚህ ማዕከል ውስጥ በነበሩበት ወቅት በርካታ ምስጢራዊ መረጃዎችን ከኢትዮዽያ መንግስትም ሆነ ሌሎች የነፃነት ታጋዮች ጋር ይለዋወጡ እንደነበር አስረድተዋል።

በማዲባ ስም የሚሰየመው ሙዚየምን የቱሪስት መስዕብ በማድረግ በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ያሳድገዋል ሲሉ አፊሰሩ መግለጻቸውን ዘገባው አመልክቷል።

ቦታውን በማንዴላ ስም ለመሰየም የኢትዮዽያ መንግስት መስማማቱን በኢትዮዽያ ኤምባሲ የፖለቲካና ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ሃላፊ ዮሃንስ አልጣሞ ተናግረዋል።

“የሃገር ውስጥም ሆነ አለም አቀፍ ጎብኚዎች መጥተው ቦታውን በመጎብኘት ከኔልሰን ማንዴላ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን እንዲያውቁ እንፈልጋለን።”በማለት አቶ ዮሃንስ አክለዋል።

ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የተውጣጡ የደቡብ አፍሪካ ሃገራትጋዜጠኞች ማዲባ ውይይት የሚያደርግባቸውና ወታደራዊ ልምምድ የሚያከናውንባቸውን ቦታዎች ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ድረ ገፁ ጠቁሞ የታጋዩ የመኝታ ክፍል የነበረው በአሁኑ ወቅት በቢሮነት እያገለገለ እንደሚገኝ አስነብቧል።

“ማንዴላ እዚህ በነበረበት ወቅት አካባቢው እንደዚህ አልነበረም፤በጊዜ ብዛት የተለወጡ ነገሮች ይታያሉ፤በእኛ በኩል የራሳችንን ዋጋ ለመከፈለ ተዘጋጅተናል፤የደቡብ አፍሪካ መንግስት ደግሞ የራሱን ሚና ሊጫወት ይገባል።” በማለት በደቡብ አፍሪካ የኢትዮዽያ አምባሳደር ሙሉጌታ ከሊል ተናግረዋል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በበኩላቸው “ታላቁ የነፃነት ተጋይ ኔልሰን ማንዴላ ወታደራዊ ስልጠና ወደወሰደበት ማዕከል መጥታችኋል፤በታሪከ መፅሃፍት ውስጥ ታሪኩን አንብባችሁ ሊሆን ይችላል፤ታሪኮቹንም እንረሳቸውም፤ለሌሎች ልናጋራቸው ከምንፈልጋቸው ታሪኮች መካከል ናቸው።” በማለት ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy