Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ረዘም ላለ ጊዜ ቴሌቪዥን በመመልከት የሚያሳልፉ ህጻናት ለአይነት 2 የስኳር በሽታ ይጋለጣሉ – ተመራማሪዎች

0 1,105

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ረጅም ሰዓት ቴሌቪዥን መመልከት ሞባይልን ጨምሮ የተለያዩ ጌሞችን እየተጫወቱ ማሳለፍ የህጻናት ተመራጩ ጊዜ ማሳለፊያ ነው።ህጻናቱ ለእነርሱ በዚህ መልኩ ጊዜያቸውን ከማሳለፍ የበለጠ ደስታን የሚፈጥርላቸው ነገር አይኖርም።

በዚህ መልኩ በቀን ውስጥ በርካታ ጊዜያቸውን በመሰል ተግባራት ያሳልፈሉ፤ ይሁን እንጅ ይህን መሰሉ ተግባር ጉዳት አለው እያሉ ነው የጤና ባለሙያዎች።በሃገረ እንግሊዝ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በዚህ መልኩ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉ ህጻናት ለአይነት ሁለት የስኳር በሽታ (ታይፕ 2 ዲያቤቲስ) ይጋለጣሉ።

በጥናቱ መሰረት ህጻናቱ በቀን ከሶስት ሰዓታት በላይ ለሆነ ጊዜ በዚህ መልኩ ማሳለፋቸው ለዚህ በሽታ ያጋልጣቸዋል።ይህ ደግሞ ከመቀመጥ ብዛት በሰውነት ውስጥ ያለው ቅባት እንዲከማች እድል ስለሚያገኝ መሆኑንም ነው ተመራማሪዎቹ የሚናገሩት።

በዚህ ሳቢያም ሰውነት በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለማመጣጠን ይቸገራል ይህ ደግሞ ለችግሩ መንስኤ መሆኑንም ይገልጻሉ።ተመራማሪዎቹ እድሜያቸው ዘጠኝ እና አስር የሆኑ 4 ሺህ 500 ህጻናትን በጥናታቸው አካተዋል።

በጥናቱም ታዲያ የህጻናቱ የኮሊስትሮል መጠን፣ በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን፣ የደም ግፊታቸው እና ሌሎች ተዛማጅ የጤና እክሎችም ተፈትሸዋል።

ህጻናቱ አዋዋላቸውን በተመለከተም ክትትል ተደርጓል፤ አራት በመቶ ያክሉ ቴሌቪዥን የማይከታተሉና ምንም አይነት የኤሌክትሮኒከስ መሳሪያ የማይጠቀሙ ናቸው። ከ1/3ኛ ከፍ ያሉት በቀን ወስጥ ለአንድ ሰዓት ያክል ቴሌቪዥን የሚከታተሉ ህጻናት ሆነው ተገኝተዋል።

28 በመቶ ያክሉ ደግሞ በቀን እስከ ሁለት ሰዓት ቴሌቪዥን መስኮት ላይ የሚያፈጡ ሲሆን፥ 13 በመቶ ያክሉ ደግሞ በቀን ውስጥ ሶስት ሰዓታት ያክል ቴሌቪዥን ላይ ጊዜያቸውን ያጠፋሉ።

18 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በቀን ከሶስት ሰዓታት በላይ የሚሆነውን ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት እና ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን በመጠቀም ጊዜያቸውን እንደሚያሳልፉ በጥናቱ ተዳሷል።በዚህም ሶስት ሰዓት እና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ጊዜያቸውን በቴሌቪዥን መስኮት እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን በመጠቀም የሚያሳልፉት ለዚህ ችግር መጋለጣቸውን አይተናል ብለዋል።

ለዚህም የቆዳቸው መለጠጥ (የውፍረት ምልክት)፣ የቅባት ከምችትን በሚያሳይ መልኩ የሰውነት ውፍረት መጨመር እና መሰል ምልክቶች መታየታቸውንም ጠቅሰዋል።ከዚህ ባለፈም ህጻናቱ በዚህ ሳቢያ የሌፕቲን መጠናቸው ይጨምራል ነው ያሉት ተመራማሪዎቹ፤ ሌፕቲን የመመገብ ፍላጎትን የሚወስንና የሚቆጣጠር ሆርሞን ነው።

እናም የህጻናቱን ለአይነት 2 የስኳር በሽታ የመጋለጥ እድላቸውን ያለ እንቅስቃሴ የሚያሳልፉትን ጊዜ በመቀነስ ማስወገድ ይገባልም ብለዋል ተመራማሪዎቹ።
ምንጭ፦ ኢንዲፔንደንት

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy