Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ስማርት የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

0 577

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየውን የመኪና ማቆሚያ ቦታ እጥረት እንደሚፈታ የታመነበት ስማርት የመኪና ማቆሚያ በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

መገናኛ አካባቢ 140 መኪኖችን የሚያስተናግደው እንዲሁም ወሎ ሰፈር የተገነባው እና 50 መኪኖችን የማስተናገድ አቅም ያለው የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ግንባታ ተጠናቆ በቀናት ውስጥ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ስማርት የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት ከመደበኛው የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት የሚለየው ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀሙ፣ በምቾቱ፣ በአስተማማኝነቱና የተሻለ ቦታ አጠቃቀምን አካቶ በመያዙ እንደሆነ ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡

የመገናኛው የመኪና ማቆሚያ ስፍራ በአንድ ጊዜ 90 መኪኖችን ወደ ላይ በኤሌክትሮ ሜካኒካል ቴክኖሎጂ በማንሳት ለማስተናገድ የሚያስችል ሲሆን በመደበኛ መኪና ማቆሚያ 9 መኪኖችን ብቻ በሚያስቆም ስፍራ ላይ 90 መኪኖችን ለማስተናገድ ያስችላል፡፡ በዛው ስፍራ 50 መኪኖችን በወለል ላይ በተሰራ የመኪና ማቆሚያ ያስተናግዳል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን ላይ ከሚገኙት 60 ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች ውስጥ በጥናት ተለይተው ደረጃ በደረጃ አስቸኳይ መፍትሄ በሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች እንደሚገነቡ የአዲስ አበባ አስተዳደር የትራንፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት የመሰረተ ልማት ክፍል ሀላፊ የሆኑት አቶ ትንሳኤ ወ/ገብርኤል አብራርተዋል፡፡

በተለያዩ የመዲናይቱ አካባቢዎችም በጨረታ ሂደት ላይ የሚገኙ፣ የዲዛይንና የግንባታ ስራቸው የተጀመረ እና በርካታ መኪኖችን ማስተናገድ የሚያስችሉ ስፍራዎች በግንባታ በሂደት ላይ እንደሚገኙ የኤጀንሲው የፓርኪንግ ማስፋፊያና ፍቃድ አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት መሪ ማእርነት ገ/ፃዲቅ ገልፀዋል፡፡

በሾላ ገበያ እና ሜክሲኮ አካባቢ 1000 መኪኖችን የሚያስተናግድ የማቆሚያ ስፍራ፣ በቸርችል ጎዳና 120 መኪኖችን የሚያስተናገድ የማቆሚያ ስፍራ፣ በመርካቶ 175 መኪኖች የሚያስተናግድ እንዲሁም ራስ መኮንን ድልድይ አካባቢ 208 መኪኖችን የሚያስተናግዱ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በዲዛይንና ግንባታ ሂደት ላይ ናቸው፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy