Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በሁከትና ብጥብጥ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች ታርመው ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉ ለሰላምና መረጋጋቱ አስተዋጽኦ አድርጓል

0 311

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በሁከትና ብጥብጥ የተሳተፉ ከ20 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎችን ከማሰር ይልቅ ታርመው ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉ ለሰላምና መረጋጋቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ መፍጠሩን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አስታወቀ።

ከስድስት ወር በፊት በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረውን ሁከት ተከትሎ፥ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰላምና ጸጥታውን ለማስጠበቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ በስራ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ሰባት አባላት ያሉትና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም የሚከታተልና የሚቆጣጠር መርማሪ ቦርድ ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል።በዛሬው ዕለትም መርማሪ ቦርዱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርቱን ያቀረበ ሲሆን፥ ተጠርጣሪዎችን መለየት፣ ማሳወቅና የሚቆዩበት ስፍራን ተመልክቶ መስተካከል ያለባቸውን እንዲስተካከሉ ማሳሰቡን በሪፖርቱ አስቀምጧል።

በዚህ ረገድ በሁለት ዙር በተደረገው ክትትልና ቁጥጥር በመጀመሪያው ዙር ከነበሩት ችግሮች በሁለተኛው ዙር በርካታ መስተካከሎች ተደርጎባቸው እንዳገኘም ነው መርማሪ ቦርዱ በሪፖርቱ የጠቆመው።

በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ ክልልና አዲስ አበባ ከተማ ላይ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ 26 ሺህ 130 ተጠርጣሪዎች ሲሆኑ፥ ከእነዚህ ውስጥ 475ቱ በምክር ተለቀዋል።

4 ሺህ 996ቱ ደግሞ ለህግ የሚቀርቡ ሆነው በመለየታቸው በዛ ልክ እየተስተናገዱ መሆኑ ተገልጿል፤ መርማሪ ቦርዱ 20 ሺህ 659 ተጠርጣሪዎች ተሃድሶ ወስደው እንደተሸኙ ማረጋገጡንም በሪፖርቱ ገልጿል።ቦርዱ በሪፖርቱ ተጠርጣሪዎችን ከማሰር ይልቅ ታርመው ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉ ለሰላምና መረጋጋቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ፈጥሯል ሲልም አስቀምጧል።

ከዚህ በተጓዳኝ ግን ህዝቡ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ካለው ጠቀሜታ አንጻር፥ እንዲቀጥል ፍላጎት ማሳየቱንም ነው የገለጸው።

አዋጁ አሁንም በስራ ላይ እንደመገኘቱ፥ ልዩ ትኩረት ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ከምግብ አቅርቦትና ከህክምና አገልግሎት ጋር በተያያዘ ጥንቃቄ እንዲደረግ፣ የመረጃ አያያዝና ልውውጥ ስርዓቱን ማጠናከርና ወደማዕከላቱ የሚላኩ ተጠርጣሪዎችን ከማዕከላቱ የመያዝ አቅም ጋር የተጣጣመ ማድረግ በቀጣይ ሊስተካከሉ እንደሚገባም አንስቷል።

ቦርዱ በተሃድሶ የተመለሱት ታራሚዎች አይደገምም በሚል መፈክር ያወደሟቸውን ተቋማት መልሰው በመገንባት ላይ እንደሚገኙም በሪፖርቱ ጠቅሷል።

ከዚህ ባለፈ ግን በቂም በቀል የተያዙና ተሸፋፍነው የታለፉ ተጠርጣሪዎች ላይ ማጣራት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሶ፥ በሂደቱ ያሉ ችግሮችን በማጥራት ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራር መኖሩንም በምላሹ አብራርቷል።

መንግስት የፊታችን ሀሙስ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ አስተያየትና ምላሽ የሚሰጥ ሲሆን፥ ስለ አዋጁ መራዘምና አለመራዘምም ማብራሪያ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። FBC

 

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy