Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በመዲናዋ ቆሼ አካባቢ በተከሰተው አደጋ የሟቾች ቁጥር 65 መድረሱ ተገለጸ

0 295

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የቆሻሻ ክምር ተንዶ የሞቱት ሰዎች ብዛት 65 መድረሱን የአስተዳደሩ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ተናገሩ።ከንቲባ ድሪባ ዛሬ ማምሻውን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ ናዳው የተጫናቸውና ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር እስከ አሁን 65 መድረሱን ተናግረዋል። አሁንም “የሟቾች ቁጥር ይጨምራል የሚል ስጋት በመኖሩ ፍለጋው ተጠናክሮ ቀጥሏል” ብለዋል።

በአደጋው እስከአሁን 20 ወንዶችና 45 ሴቶች ህይወታቸው በአሳዛኝ ሁኔታ ማለፉን የተናገሩት ከንቲባው፤ ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ የከተማው ነዋሪ እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በየእምነቱ መካነ መቃብር ሥርዓተ ቀብራቸው መፈፀሙን ገልጸዋል።ነዋሪነታቸው ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ የሆኑትንም ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በየክልሉ አስክሬን የመላክ ስራ መከናወኑንም ተናግረዋል።የአካበባቢው ነዋሪ፣ የፀጥታ ሃይሎች እንዲሁም የእሳትና ድንገተኛ ሰራተኞች የአደጋውን ስጋት ለመቀነስ በተቀናጀ ሁኔታ እየሰሩ መሆኑንም አመልክተዋል።

ለአደጋ የተጋለጡ ዜጎችን ከአካባቢው የማስነሳት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው፤ እሰከአሁን 297 ቤተሰቦችን ተጨማሪ የመሬት መደርመስ አደጋ ሊመጣ  ስለሚችል ወደ ሌላ ቦታ የማዘዋወር ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።አሁንም ተጨማሪ ለአደጋ ሊጋለጡ የሚችሉ ካሉ ጥናቶች እየተደረጉ የማንሳት ስራ እንደሚከናወን ገልጸዋል።በዘላቂነት የማቋቋም እና በጊዜያዊነት የሚያስፈልገው ምግብና ልብስ  ድጋፍ በመንግስት እየተሰጠ መሆኑን የጠቆሙት ከንቲባው፤ “የእርዳታ ሰጪ ተቋማትና ሌሎች አካላት ቢያግዙ መልካም ነው” ብለዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy