የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሚያስችል በአልኮል መጠን መመርመሪያ መሳሪያ በመታገዝ የሚያደርገውን ቁጥጥር ከነገ ጀምሮ ውጤቱን መሰረት ያደረገ እርምጃ በመውሰድ እንደሚጀምር አስታወቀ።
ኮሚሽኑ እንደገለጸው በመሳሪያ ምርመራው የተገኘውን ውጤት መሰረት በማድረግም፥ የቅጣት እርምጃ መውሰድ ይጀምራል።
በበጀት አመቱ ስድስት ወራት በ11 ሺህ 356 አሽከርካሪዎች ላይ በተደረገ ምርመራ፥ 366 አሽከርካሪዎች ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠቀማቸው መረጋገጡን ምክትል ኮሚሽነር ተስፋዬ ደንደና ተናግረዋል።
አሽከርካሪዎቹ ትምህርት በመስጠት የተለቀቁ ሲሆን፥ ከነገ ጀምሮ በተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ በሚገኙ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ በቂ ዝግጅት መደረጉንም ነው ምክትል ኮሚሽነሩ የተናገሩት።