Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በማምረቻው ዘርፍ የውጭ ባለሀብቶች ጋር ሽርክና ለሚመሰርቱ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ልዩ የድጋፍ ስርአት ተዘርግቷል- መንግስት

0 489

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አለሙ ሰሜ መንግሰት ከውጭ ባለሀብቶች ጋር ሽርክና መስርተው በማምረቻው ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች የተለየ የድጋፍ ስርአት መዘርጋቱን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ባለፉት ሁለት አመታት በሽርክና የመስራት ፍላጎቱ እየጨመረ መምጣቱን ቢጠቅስም፤ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የምጣኔ ሃብት ምሁር ለዘርፉ አሁንም በቂ ትኩረት አልተሰጠም የሚል ሃሳብ አላቸው።

ፈጣን የኢኮኖሚ ግስጋሴ ያስመዘገቡት የኤዠያ ነብሮች እየተባሉ የሚሞካሹት ሀገራት እስከ 1985 ባለው ጊዜ ገበያቸውን ለውጭ ባለሀብት ዝግ ማድረጋቸው ይህ ነው የሚባል የኢኮኖሚ እድገት እንዳያስመዘግቡ እንቅፋት ሆኖባቸዋል።

ይሁንና የማምረቻ ዘርፉን ላስቀደመ ኢንቨስትመንት በራሳቸውን ሲከፍቱ ታሪካቸው መለወጡ ይነገራል፡፡

የእነዚህን ሀገራት እድገት ያፋጠኑት ቀላል ኢንደስትሪዎች አሁን አይናቸውን አፍሪካ ላይ ጥለዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን ኮሚሽነሩ አቶ ፍጹም አረጋ ይህ በርካታ የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ላይ ላለችው ኢትዮጵያ መልካም እድል ነው ይላሉ ።

ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ጋር መስማማት እና የፋብሪካ አዲስነት ኢትዮጵያ የውጭ ባለሀብቶችን የምትቀበልበት መስፈርት መሆኑን የገለጹት አቶ ፍጹም፤የሚነሱ ክፍተቶች እንደተጠበቁ ሆነው እስካሁን ወደ ሀገሪቱ የገቡ ኢንደስትሪዎች ራሳቸውን ከህጉ ጋር ለማጣጣም የሞከሩ ናቸው።

ሀገሪቱን በአመት እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን እሰከ መሳብ የደረሰ ውጤት አስመዝግባለች።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ መምህሩ አቶ ምትኩ ከበደ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፤ ፍሰት መጨመር፤የጥቅሙን ያህል ሀገራትን የውጭ በላሀብቶች ጥገኛ የማድረግ ጉዳት እንዳለበት ያነሳሉ።

ኢትዮጵያም የውጭ እና የሀገር ውስጥ በለህብቶችን ተሳትፎ ሚዛናዊ አደርጋ መሄድ አለባት የሚል ሃሳብ አላቸው።

መንግስትም ኢትዮጵያ በውጭ ባለሀብቶች እንድትጥለቀለቅ እና የውጭ ባለሀብቶች ጥገኛ እንድትሆን ፍላጎት እንደሌለው በተለያዩ ጊዜያት ሲገልጽ ይሰማል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር አለሙ ሰሜ፤ለዚህ የሀገር ወስጥ ባለሀብቶች የተለየ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ስርአት መዘርጋቱን ተናግረዋል፡፡

በዚህም የብድር አቅርቦቱን በማሻሻል ፤ 25 በመቶ ማስያዝ ለሚችሉ የሀገር ውስጥ ባለሀብት የ75 በመቶ ብድር አመቻችቶአል።

ለኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ለሚገቡት የብድር አቅርቦቱ 85 / 15 ሆኖአል።

ከዚህ ባሸገር የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የቴክኖሎጂ አቅማቸውን እና የገበያ ድርሻቸውን ለማስፋት ከውጭ ባለሀብቶች ጋር የሚሰሩበት መንገድ ተመቻችቶአል ይላሉ ዶክተር አለሙ፡፡

የገሊላ ኢንዱስትሪያ ኢንጂነሪንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ባለቤት አቶ ገብረህይወት ገብረ እግዚአብሄር እንደተናገሩት ፤ከውጭ በለሀብቶች ጋር ሽርክና በመፍጠራቸው በአመት ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ዶላር ትርፍ የሚያገኝ ኢንቨስትመንት ባለቤት ሆነዋል፡

ከስምንት አመታት በፊት ኩባንያቸውን ያቋቋመው የቱርኩ ሳይድሩ ዲዛይን በስሩ 900 ኢትዮጵያውያንን ቀጥሮ ያሰራል።

ከአንድ ኢትዮጵያ ባለሀብት ጋር በሽርክና ስራ የጀመሩት የድርጅቱ ባለድርሻ ሰርካን መህመት ዱሩ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ መዋእለ ነዋይ የሚያፈሱ የውጭ ባለሀብቶች ትልቁ አዋጪ መንገድ ከኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ጋር በሽርና መስራት ነው።

በኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ምስግና እንደሚናገሩት ፤እንደመንግስትም እንደ ዘርፍ የሽርክና አሰራር ከተመቻቸ 2 አመታትን አስቆጥሯል፡፡

የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ከውጭ ሀገራት ጋር የመስራት ፍላጎት መጨመሩን የጠቀሱት አቶ ቢኒያም፤ይሁንና በሽርክና ማምረቻው ዘርፍ ከመስራት ይልቅ በውጪ ሀገር ያመረቱትን ቁሳቁስ አከፋፋይ የመፈለግ ፍላጎት አሁኑም ሰፊ ፈተና ነው።

ሀገሪቱ የምትፈልገውን ያህል በማምረቻ ዘርፍ ላይ የተሰማራ ባለሃብት ለማግኘት የሰው ምርትን አምጥቶ ከማከፋፈል የራስን ወደ ማምረት የሚመጣ ባለሀብት ያስፈልጋታል ብለዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy