Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተሳሳተ መረጃ እንዳይታለሉ ሚኒስትሩ አስጠነቀቁ

0 621

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በሳዑዲ የሚኖሩ ዜጎች በተሳሳተ መረጃ እንዳይታለሉ ሚኒስትሩ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ አስጠንቅቀዋል፡፡

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ከመጋቢት 20 ጀምሮ በ90 ቀናት ውስጥ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው የማናቸውም ሀገራት ዜጎች እንዲወጡ የእፎይታ ጊዜ ሰጥቷል ነው ያሉት፡፡

በዚህ የእፎይታ ጊዜ ያፈሩትን ሀብትና ንብረት ይዘው እንዲወጡ በተወሰነው መሰረት ኢትዮጵያዊያን በሰላም እንዲወጡ መንግስት በሳዑዲ ከሚገኘው ኤምባሲ ጋር በመነጋገር ሁኔታዎችን አመቻችቷል ብለዋል፡፡

“የአረብ ሀገራት መንግስታት ህግ ያወጣሉ እንጂ አይተገብሩም፤ ኢትዮጵያ ሄዳችሁ ምን ታደርጋላችሁ!” የሚሉ የተሳሳቱ መረጃዎች እየተናፈሱ በመሆኑ ዜጎች በዚህ መረጃ ሳይታለሉ በእፎይታ ጊዜ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አስገንዝበዋል፡፡

በሳዑዲ ዓረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሰላም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መንግስት ዝግጅት ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

በሀገር ውስጥም ጉዳዩን የሚከታተል ግብረ-ሀይል እንዲሁም ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ ስራ መጀመሩን አረጋግጠዋል ፡፡

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ጉዳዩን እየተከታተለ ለህብረተሰቡ መረጃ እንደሚያቀርብ ዶክተር ነገሪ በዛምቢያ ጉብኝት እያደረጉ ባሉበት ወቅት ገልፀዋል-(ኢብኮ) ፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy