Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በሴቶችና ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ አፍሪካውያን ከኢትዮጵያ ሊማሩ ይገባል-አፍሪካውያን ጋዜጠኞች

0 748

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ ለወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ፈጠራ የምታደርገው እንቅስቃሴ ልምድ ሊወሰድበት እንደሚገባ አፍሪካውያን ጋዜጠኞች ተናገሩ።ከደቡብ አፍሪካ፣ ሞዛምቢክና ቦትስዋና የመንግስትና የግል የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የተውጣጡ 15 ጋዜጠኞች ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ጋዜጠኞቹ ከጎበኟቸው የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች መካከል የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ፣ የቦሌ ለሚና የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርኮች  ይገኙበታል።

በጉብኝታቸው ኢትዮጵያ ለወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ የምታደርገውን እንቅስቃሴና ሴቶች በማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ያላቸውን ተሳትፎ አድንቀዋል።በዚህ ረገድ ሌሎች አገራት ከኢትዮጵያ ተሞክሮ ልምድ ሊወሰዱ እንደሚገባ ነው ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡት።

ከደቡብ አፍሪካ ኤ ኤን ኤን 7 የመጣችው ጋዜጠኛ ካልዴን ኦንግሙ በኢትዮጵያ የሚገኙ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ሴቶችን ሲያሳትፉ በማየቷ ትልቅ ኩራት እንደተሰማት ነው የተናገረችው።

ከደቡብ አፍሪካ ሲቲ ፕሬስ ጋዜጣ የመጣችው ጋዜጠኛ ስቴምብል ሴሌም ኢትዮጵያ ለሴቶች የሰጠችው ትኩረት በሌሎች አፍሪካውያን አገራት ዘንድ የተለመደ አይደለም ስትል ነው ያብራራችው።

ደቡብ አፍሪካም ሆነ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ይህን ተሞክሮ ሊወስዱ እንደሚገባ ጋዜጠኛዋ ተናግራለች።

ታቦ ክሌመንት የመጣው መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ካደረገው 702 ከተሰኘ ራዲዮ ጣቢያ ነው።

እንደ ክሌመንት ገለጻ በኢትዮጵያ ያለው የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴ የሚበረታታ በመሆኑ ትምህርት ሊወሰድበት የሚችል ነው።

በሚሰሩ ፕሮጀክቶች ለሴቶች ቅድሚያ በመስጠት ረገድም ከኢትዮጵያ መማር እንደሚያስፈልግ ነው ክሌመንት አስተያየቱን የሰጠው።

ኢ ሲ ኤን የተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያን ወክላ የመጣችው ሲቄሌሌዋ ምድምጊ በበኩሏ በአገሯ በደቡብ አፍሪካ የሴቶች ተሳትፎ ዛሬም ድረስ ችግር አለበት ባይ ናት።

በኢትዮጵያ የሚታየው የሴቶች ተሳትፎ ግን የሚያስደንቅ እንደሆነ ተናግራለች።

ጋዜጠኞቹ ከማምረቻ ኢንዱስትሪዎች በተጨማሪ የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመርን፣ የየካ አባዶ የጋራ መኖሪያ ቤቶችና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን መጎብኘታቸው ይታወሳል። ENA

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy