Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በቆሻሻ ክምር መደርመስ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ከነገ ጀምሮ ጸሎተ-ፍትሐት ይደረጋል

0 318

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቆሼ በተሰኘው አካባቢ በደረሰ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ከነገ ጀምሮ ጸሎተ-ፍትሐት እንደሚደረግ ገለጸች።

ቤተክርስቲያኗ በአደጋው ለተጎዱና መጠለያ ላጡ ወገኖች የሚውል የ200 ሺህ ብር እርዳታ እንዲሰጥ መወሰኗንም አስታውቃለች።ቤተክርስቲያኗ በአዲስ አበባ መጋቢት 2 ቀን 2009 ዓ.ም ምሽት ዜጎች ላይ በደረሰው የሞተ አደጋ የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ገልፃለች።
“በደረሰው ሕልፈተ ሕይወት ለተጎዱ ቤተሰቦች እግዚአብሔር አምላክ መጽናናትና ብርታትን እንዲሰጥ፤ የሟቾችንም ነፍስ በመንግስቱ እንዲቀበል ፀሎት ይደረጋል” ስትልም በመግለጫው አመልክታለች። ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy