Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአስረኛው የአዲስ አበባ መሪ እቅድ ፕሮጀክት ለእግረኛ መንገድ ትኩረት መሰጠቱ ተገለጸ

0 498

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአስረኛው የአዲስ አበባ መሪ እቅድ መሠረት የሚገነቡ መንገዶች የእግረኛ መንገድ በማስፋት ሽፋኑን ለማሳደግ ትኩረት የሰጠ መሆኑን የአዲስ አበባ መሪ ፕላን ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ገለጸ።በመሪ እቅዱ የመዲናዋ የመንገድ መሠረተ ልማት 30 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 60 በመቶ የሚሆነው የእግረኛ መንገድ ነው ተብሏል።ጽህፈት ቤቱ በመሪ እቅዱ ፕሮጀክት የመንገድ ዘርፍ አተገባበር ባስጠናቸው እቅዶች ላይ ከአስፈጻሚ አካላት ጋር ዛሬ አውደ ጥናት አካሂዷል።

በአውደ ጥናቱ ላይ በአምስትና በአስር ዓመቱ የአዲስ አበባ መሪ እቅድ ፕሮጀክት ስልታዊ የልማት እቅድ ትግበራ መካከል ቅድሚያ ከተሰጣቸው ተግባራት የመንገድና መጓጓዣ አንዱ መሆኑ ነው የተገለጸው።

የመዲናዋ የትራፊክ ፍሰት እንዲሳለጥና የትራፊክ አደጋን በግማሽ ለመቀነስ ከተቀየሱ ተግባራት መካከል ለእግረኛ መንገድ ሰፊ ሽፋን መስጠት እንደሆነም ተመልክቷል።

በፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ የትራንስፖርትና መንገድ ጥናት ባለሙያ አቶ ጋሻው አበራ፤ ከዚህ በፊት በተከናወኑ የመንገድ ግንባታዎች ለእግረኛ መንገድ ትኩረት ሳይሰጥ መቆየቱን ገልጸው፤ “በ10ኛው መሪ እቅድ የመንገድ የጎንዮሽ እይታን ማስፋት ትኩረት ተደርጎበታል” ብለዋል።

በዚህም በአዲሱ መሪ እቅድ በሚዘረጉ መንገዶች 60 በመቶው ለእግረኛ መንገድ ሽፋን የሚተው መሆኑን ገልጸዋል።መርካቶን በመሳሰሉ ዋና ዋና የህዝብ መንቀሳቀሻ ማዕከላትና የገበያ ቦታዎችም የእግረኛ መንገዶች በጥናት መለየታቸውን ነው የተናገሩት። ይህ በእንዲህ እንዳለ በመሪ እቅዱ የትራፊክ ፍሰቱን መጨናነቅ ለማቃለል ሰባት የጭነት ተሽከርካሪ ትራንስፖርት መነኸሪያዎች በጥናቱ ተለይተዋል።የጭነት ተሽከርካሪዎች በየትኛው ሰዓት በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ በመደንገግ  የሰዓት ገደብ እንደሚበጅላቸውም ተገልጿል።የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ ማዕከላዊ መነኸሪያ፣ የከተማ ውስጥና የክልል የሕዝብ ትራንስፖርት መነኸሪያዎች ተብለው በጥናት ተለይተዋል።

ተሽከርካሪዎች በአውራ መንገዶች ላይ እንዳይቆሙ ለማድረግም በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች 66 የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች ወይም ፓርኪንጎች በጥናቱ እንደተለዩም ተገልጿል።

በአስር ዓመቱ መሪ እቅድ ፕሮጀክት 330 ኪሎ ሜትር መንገዶችና 47 ልዩ መንገዶች የሚገነቡ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ 27 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ ተገምቷል።በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ሦስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ተጓዥ የጉዞ ፍላጎት መኖሩን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy