Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአዲስ አበባ “ቆሼ” በሚባለው አካባቢ የቆሻሻ ክምር ተደርምሶ እስካሁን የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል

0 1,207

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአዲስ አበባ “ቆሼ” በሚባለው አካባቢ የቆሻሻ ክምር ተደርምሶ እስካሁን የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ስሙ ቆሼ ተብሎ በሚራው አካባቢ የቆሻሻ ክምር የመደርመስ አደጋ የተከሰተው ትላንት ምሽት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ ነበር፡፡
አደጋው በመኖሪያ ቤቶች ላይ የደረሰ በመሆኑ ለሰው ህይወትና ንበረት መጥፋት ምክንያት ሆኗል፡፡
ከአደጋው የተረፉ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ሙሉ ንብረቶቻቸውና የሰው ህይወት ጉዳትና መጥፋት እንደገጠማቸው ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማ አደጋው በደረሰበት ቦታ ተገኝተው እንዳሉት በአደጋው ምክንያት እስካሁን የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው 37 ሰዎች በአለርት ሆስፒታል ህክምና በመከታተል ላይ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡
የአይን እማኞች ለኢቢሲ እንደተናገሩት ግን ከአደጋው ከባድነት አንፃር የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ ይችላል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy