Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአዲስ አበባ በቀጣይ ሁለት ወራት 20 ሺህ ወጣቶች ወደ ስራ ይገባሉ

0 1,034

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአዲስ አበባ በመጀመሪያው ዙር ተመዝግበው በስልጠና ላይ የሚገኙ 20 ሺህ ወጣቶች በቀጣይ ሁለት ወራት ወደ ስራ ይገባሉ ተባለ።ከተመደው የ10 ቢሊየን ብር ተንቀሳቃሽ ፈንድ ከ419 ሚሊየን ብር በላይ የደረሰው የከተማው አስተዳደር የወጣቶችን ችግር ለመፍታት የተያዘውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ በከንቲባው የሚመራ ኮማንድ ፖስት አቋቁሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው እንደገለጹት፥ በመጀመሪያው ዙር 20 ሺህ ወጣቶች ተለይተው ወደ ስልጠና ገብተዋል።

ስልጠናው በ30 ኮሌጆችና ማሰልጠኛ ተቋማት እየተሰጠ ሲሆን 66 የሙያ ዘርፍ አማራጮችም ተለይተው ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ተግባር መገባቱን ሀላፊው ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ቴከኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘሩ ስሙር በበኩላቸው፥ የከተማ ግብርና፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ፣ የኢኮኖሚ መሰረተ ልማት፣ የምግብ ዝግጅትና ንግድ ከተለዩት የልማት ዘርፎች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

ዘርፎቹ በስራቸው ዝርዝር አማራጮች ተቀምጦላቸው ወጣቶቹ ወደ መጀመሪያው ዙር ስልጠና እንዲገቡ መደረጉን አቶ ዘሩ ጠቁመዋል።ሰልጣኞቹ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት እንደየዘርፋቸው ስልጠናቸውን እየጨረሱ ያለምንም ወጪ ምዘና የሚሰጣቸው ይሆናል።በምዘናው መሰረት ክፍተት ያለባቸው ሰልጣኞች ዳግም የክፍተት መሙያ ሰልጠና እንዲያገኙ ይደረጋል ነው የተባለው።

ውጤታማ ስራ እንዲሰራ ከአምስት ቢሮዎች ተወጣጥቶ የተመሰረተው ኮማንድ ፖስትም የማምረቻና መሸጫ ቦታ፣ የገንዘቡ አቅርቦት፣ የተለያዩ የቢዝነስ እቅዶችና መሰል ስራዎች ከወዲሁ እንዲዘጋጁ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።FBC

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy