Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት የተሰማሩ አውሮፓውያን ባለሀብቶች የቢዝነስ ፎረም አቋቋሙ

0 566

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ የተሰማሩ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ባለሀብቶች የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ አቋቁመዋል።

ፎረሙ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ላይ መዋእለ ነዋያቸውን እያፈሰሱ ያሉ የህብረቱ አባል ሀገራት ኩባንያዎች በሚያጋጥሟቸው ችግሮች እና ኢንቨስትመንታቸውን በሚያስፋፉባቸው ጉዳዮች ላይ ለመምከር የሚያስችል ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍፁም አረጋ በፎረሙ ላይ እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያ ለዓለም ሀገራት ምቹ የኢንቨሰትመንት አማራጭ ለመሆን የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች፡፡

ኮሚሽነሩ ሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ገንብታ ለኩባንያዎች ክፍት እያደረገች መሆኗንም ጠቁመዋል።

የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ኩባንያዎች ኢትዮጵያ አመቺ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን አንስተው፥ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ ኢንቨስት እያደረጉ ያሉ ባለሀብቶችም ከኢንቨስትመንታቸው ጋር ተያይዞ ለሚኖራቸው ማንኛውም ጥያቄ የቢዝነስ ፎረሙ መቋቋሙ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው ነው የገለፁት።

በአበባ ልማት ዘርፍ በርካታ የአውሮፓ ኩባንያዎች ተሰማርተው ውጤታማ መሆናቸውን ባለሃብቶቹ አንስተዋል።

በቀጣይም ዘርፉን በእጥፍ ለማሳደፍ 5 ሺህ ሄክታር መሬት የተዘጋጀ ሲሆን፥ የሻሸመኔ፣ ሃዋሳ፣ ባህርዳር እና ወላይታ አካባቢዎች ለስራው መመረጣቸውን ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት።

የአውሮፓ ህብረት እና ኢትዮጵያ ከግማሽ ክፍለ ዘመን ባለይ የዘለቀ የንግድ ትብብር እና የኢኮኖሚ ወዳጅነት አላቸው።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy