Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በኦሮሚያ ክልል ከ8 ሺህ በላይ ወጣቶች ማዕድን በማምረት ስራ ላይ ተሰማሩ

0 444

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኦሮሚያ ክልል ከ8 ሺህ በላይ ወጣቶች ማዕድን በማምረት ስራ ላይ መሰማራታቸው ተገለፀ።ወጣቶቹ መንግስት ባመቻቸው የማዕድን ዘርፍ በምስራቅ ሸዋ፣ በአሪሲ ዞን እና በቢሾፍቱ ተደራጅተው ነው ወደ ስራ የገቡት።

የክልሉ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃብታሙ ሃይለሚካኤል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የክልሉ መንግስት ከፌዴራል መንግስት ጋር በመተባበር ባመቻቸው ማዕድን የማምረት ዘርፍ ወጣቶቹ ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ስራ ገብተዋል።

ለፋብሪካ ሲሚንቶ ግብአት የሚረከቡ እንደ ደርባ እና ዳንጎቴ የመሳሰሉት ድርጅቶች ለወጣቶቹ የማምረቻ ማሸነሪ ግብአት ማቅረባቸውንም ነው ሀላፊው የገለጹት።

በዚህ መልኩ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በኮንስትራከሽን፣ በግብርና፣ በማምረቻ እና በሌሎችም በተለያዩ ዘርፎች ለ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ህዝቡን ያሳተፉ የልየታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል አቶ ሃብታሙ።በዚህ የልየታ ስራም እስካሁን ከ900 ሺህ በላይ ወጣቶች ተለይተዋል ነው ያሉት።

ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ በፌዴራል መንግስት 3 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ከተበጀተው ተዘዋዋሪ ፈንድ ባሻገር ክልሉም 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መድቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ጠቁመዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy