Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በየክልሎቹ የሚዘዋወረው አዲስ የንቅናቄ ችቦ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ያስችላል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

0 378

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን በተግባር በመተርጎም የጸረ ድህነት ትግሉን በስኬት ለመወጣት በየክልሎቹ የሚዘዋወረው የትውልድ ቅብብሎሽ ማሳያ የሆነው አዲስ የንቅናቄ ችቦ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚያስችል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስታታወቁ።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፤ የአድዋ ድል ታሪክ ጥልቅ ሀሳብ በትውልድ ቅብብሎሽ በጸረ ድህነት ዘመቻው በመረባረብ ውጤማነቱ እንዲቀጥል ማድረግ ያስፈልጋል። ለዚህም በ121ኛ የአድዋ ድለ መታሰቢያ በዓል በታሪካዊው ቦታ በተከበረበት ወቅት የትውልድ ቅብብሎሹ ማሳያ የንቅናቄ ችቦ ርክክብ ተደርጓል።“የታላቁ ህዳሴ ግድባችን ብሄራዊ መግባባት መሰረት የተጣለበት አንድ ብርቅዬ ፕሮጀክታችን ነው” ያሉት አቶ ደመቀ፤ ክልሎች በየተራ የሚረከቡትን ችቦ ጨምሮ ህብረተሰቡ ግለቱን አጎልብቶ ለላቀው ምዕራፍ በቦንድ ግዥና በምክረ ሀሳብ የባለቤትነት ተሳትፎውን ማጠናከር የሚያስችሉ ዝግጅቶች እየተካሄዱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።“የችቦ ቅብብሎሹን በቦንድ ግዥ፣ በአጋርነትና በባለቤትነት አጠናክሮ ለመቀጠል ይፋ ሆኖ በሚወጣው መርሃ ግብር መሰረት ተረካቢ ክልሎች ለኩሰው ይቀጥላል” ብለዋል።የዚህ ዓይነቱ ንቅናቄ የህዝቡን ግለት ወደ ጋራ መድረክ የሚያወጣ ተሳትፎን የሚያጠናክር መሆኑንም ገልጸዋል።የታላቁ ህዳሴ ግድብ የብሄሮች ብሄረሰቦችና ሕዘቦች ዋንጫ በየክልሉ በተንቀሳቀሰበት ወቅት ህዝብ ከህዝብ ከማስተሳሰር ባሻገር በቦንድ ግዥ ታሪክ መሰራቱን አስታውሰው፤ አሁንም ዋንጫው እንደቀጠለ የንቅናቄው ችቦ በአዲስ መልክ ጉዞ እንደሚጀምር ተናግረዋል።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፤ በጸረ ድህነት ዘመቻው በሁሉም መስክ የድርሻን በማሳካት የአድዋን ገድል የትውልድ ቅብብሎሽ አደራ መወጣት አስፈላጊ ነው።የ121ኛ አድዋ ድል በዓል በታሪካዊው ስፍራ በተከበረበት ዕለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የንቅናቄውን ችቦ ለፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ለአቶ ያለው አባተ ማስረከባቸው ይታወሳል።በሌላ በኩል “ጊዜ የለንም እንሮጣለን! ለህዳሴ ግድባችን እንቆጥባለን!” በሚል መሪ ሀሳብ ነገ በሚካሄደው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሩጫ መላው ህብረተሰብ እንዲሳተፍ ጥሪ አድርገዋል።የዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ በሚካሄደው ሩጫ ላይ ሁሉም ተሳትፎ በማድረግ አጋርነቱን ማሳየት እንዳለበት አስገንዝበዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ።የዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ106ኛ በአገራችን ለ41ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሃ ግበሮች ይከበራል።ታላቅ አገራዊ የሩጫ መርሃግብር የተዘጋጀው ሴቶች የግድቡ ባለቤትነታቸው፣ ፋና ወጊነታቸው፣ ቀጣይነታቸውና ተሳትፏቸውን የበለጠ ለማጠናከር መሆኑን ገልጸዋል።የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሩጫ በመላው አገሪቷ ከተሞችና ዞኖች የሚካሄድ ሲሆን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ከሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴርና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የተዘጋጀ ነው።

ምንጭ፡- ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy