Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በድርቅና በበሽታ ምክንያት ሊጠፉ የተቃረቡ ተኩላዎች እያንሰራሩ ነው

0 735

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በድርቅና በበሽታ ምክንያት ሊጠፉ የተቃረቡ ተኩላዎች እያንሰራሩ ነው
የካቲት 24/2009 በድርቅና በበሽታ ምክንያት ሊጠፉ የተቃረቡ ተኩላዎች ቁጥር መልሶ ማንሰራራት መጀመሩን ቤልፋስት ቴሌግራፍ በድረ ገፅ ዘገባው አስነብቧል።
እንደ መረጃው 60 አዲስ የተወለዱ የተኩላ ቡችሎችን በደቡባዊ ኢትዮዽያ በሚገኘው ባሌ ተራሮች ፓርክ መመዝገቡን ዘ ቦርን ፍሪ ፋውንዴሽን የተሰኘው ግብረ ሰናይ ተቋም አስታውቋል።
በአሁኑ ወቅት በሃገሪቱ ተራሮች ላይ የሚገኙት የኢትዮጰያ ተኩላዎች ከ500 ያነሱ ናቸው ብሏል፡፡
ተኩላዎቹ በብዛት የሚገኙባቸው የባሌ ተራራሮች ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ገዳይ በሆኑ የእብድ ውሻ በሽታ፣የቫይረስ ብሎም የድርቅ አደጋ ተጠቅቶ እንደነበር ዘገባው አክሎ ጠቁሟል።
በአካባቢው ለምነት የተነሳ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ከፍተኛ ቦታዎች በመንቀሳቀስ በተክሎች ላይ ባደረሱት ጥፋት ሳቢያ የተኩላ ዝርያዎቹ የመጥፋት ስጋት ውስጥ እንዲገቡ ማድረጉን ድረ ገፁ በዘገባው ማጠቃለያ ላይ አንስቷል

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy