Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በጉጂ ዞን ድርቅ በተከሰተባቸው የአርብቶ አደር አካባቢዎች ለ171 ሺህ ተረጂዎች ድጋፍ እየቀረበ ነው

0 395

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን ድርቅ በተከሰተባቸው የአርብቶ አደር አካባቢዎች ለሚኖሩ 171 ሺህ ተረጂዎች መንግስት የምግብና የእንስሳት መኖ ድጋፍ እያቀረበ ነው።በዞኑ በክረምቱ በቂ የዝናብ ስርጭት ባለመኖሩና ቀድሞ መውጣቱን ተከትሎ፥ በ5ቱ ወረዳዎች ድርቅ ተከስቷል።የክልሉ መንግስትም በዞኑ ለተለዩ 171 ሺህ ተረጂዎች፥ የምግብ፣ የውሃ፣ የእንስሳት መኖ፣ የመድሃኒት አቅርቦትና ክትባት እየሰጠ ይገኛል።የህጻናት ምግብ፣ የእንስሳት መኖ አቅርቦት እጥረት እና የስርጭት አለመመጣጠን ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ተስተውሏል።ከዚህ ጋር ተያይዞ እርዳታው በአንዳንድ አካባቢዎች በታሰበው ፍጥነት ያለመድረስ ችግር እንደሚስተዋልበት አርብቶ አደሮች ገልጸዋል።አርብቶ አደሮቹ የክልሉ መንግስት የሚስተዋለውን ችግር በአፋጣኝ በመፍታት ምላሽ ሊሰጣቸው እንደሚገባም ነው የገለጹት።የዞኑ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አበበ አባቡልኮ በበኩላቸው፥ ከህጻናት ምግብ እና ከእንስሳት መኖ አቅርቦት ጋር ተያይዞ ችግር መኖሩን አምነዋል።ለዚህም በመንግስት ይደረግ የነበረው የአቅርቦት መቆራረጥ መንስኤ መሆኑን ጠቅሰዋል።የህጻናት ምግብ፣ የእንስሳት መኖ አቅርቦት ችግር እና የስርጭት ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑንም ሃላፊው ጠቁመዋል።በቀጣይ የበልግ ዝናብ ዘግይቶ ከገባ ችግሩ ቀጣይ እንደሚሆን የጠቀሱት ሃላፊው፥ በዞኑ ያለውን ቀጣይ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩም ለክልሉ መንግስት ጥያቄ ቀርቧል ብለዋል።እንደ ሃላፊው ገለጻ በዞኑ ከተከሰተው ድርቅ ጋር ተያይዞ ከመንግስት ባሻገር፥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የቤት ውስጥ መገልገያዎችን፣ አልባሳት፣ ድንኳን እና መሰል የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።ከዚህ በተጨማሪም ህዝቡ በቦታው በመገኘት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፥ የነገሌ ከተማ ነዋሪዎች እና የመንግስት ሰራተኞች በጉሚ ኤልዶሎ እና በሊበን ወረዳ ለሚገኙ ተረጂዎች ድጋፍ አድርገዋልም ነው ያሉት።በዚህ አመት ብቻም ከህብረተሰቡ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።ይህን መሰሉ የህብረተሰቡ ድጋፍ በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy