Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በጥር ወር ለመንግስት ሰራተኞች የተደረገው የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ወይስ የደመወዝ ጭማሪ?

0 3,469

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

መንግስት በጥር ወር 2009 ለመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ መድረጉ ይታወቃል።ይህ የደመወዝ ማስተካከያ ከዚህ ቀደም ከሌላው የመንግስት ሰራተኛ ከፍ ያለ የደመወዝ ስኬል ያላቸው ተቋማትን አይመለከትም።በዚህ የደመወዝ ማስተካከያ ያልተካተቱ የመንግስት ሰራተኞችም የተለያዩ ቅሬታዎችን እያቀረቡ በመሆኑ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር እና ትምህርት ሚኒስቴር ጋራ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ፦

የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ የሚባለው ደመወዝን ከገበያ ጋር ለማቀራረብ የመንግስትን የመክፈል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚደረግ ማሻሻያ ነው። የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ሲደረግ ቀድሞ ማስተካከያ የተደረገባቸውን ወይም የተሻለ ክፍያ የሚያገኙ ሠራተኞችን አይመለከትም። የኑሮ ውድነት ማካካሻ የሚባለው ደግሞ ወቅታዊ የገበያ ሁኔታ በሰራተኛውኑሮ ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመቅረፍ የመንግስትን የመክፈል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚደረግ የኑሮ ውድነት ማካካሻ ነው። የደመወዝ ስኬል ማስተካከያም ሆነ የኑሮ ውድነት ማካካሻ ያለፉት 10 ዓመታት ተሞክሮ የሚያሳየውበአማካይ በየሦስት ዓመቱ መደረጉን ነው።

በሌላ በኩል የደመወዝ ጭማሪ ከመደበኛ የውጤት ተኮር ምዘና ውጤት ላይ ተመሥርቶ ለአንድ ሰራተኛ ከተመደበበት የሥራ ደረጃ የጣሪያ ደመወዝ ሳያልፍ የሚደረግ መደበኛ የእርከን ደመወዝ ጭማሪ ነው። በዚህም ሠራተኛው ከነበረበትየመነሻ ወይም የእርከን ደመወዝ ወደ ቀጣዩ የእርከን ደመወዝ ላይ እንዲያርፍ የሚደረግበት አሰራር ነው።

በሐምሌ 2008 ለመምህራን የፀደቀው ማሻሻያ የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ነው። በተመሳሳይ በጥር ወር 2009 ዓ.ም.በሚኒስትሮች ምክር ቤት ለመንግስት ሰራተኞች የፀደቀውም የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ነው። ሁለቱም የደመወዝ ጭማሪአይደሉም።

በያዝነው በጀት ዓመት መጀመሪያ የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ የተደረገላቸው ተቋማት አሉ። እነዚህም ዳኞች፣ ዐቃብያነ ህግ፣ መምህራንና የአካዳሚ ሠራተኞች እና የገቢዎችና ጉምሩክባለሥልጣን ናቸው፡፡ ከአገሪቱ ኢኮኖሚና የመክፈል አቅም ጋር እንዲሁም ከአሰራር አኳያ የስኬል ማስተካከያ በየመንፈቅአመቱ ሊካሄድ የሚችል ባለመሆኑ እነዚህ ተቋማት በአሁኑ ስኬል ማስተካከያ አልተካተቱም፡፡

በተመሳሳይ ቀድሞውንም የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ የተደረገላቸውና በልዩ ስኬል የዓላማ ፈፃሚዎች ደመወዝ ስኬልእየተስተናገዱ የነበሩና በአንፃራዊ መልኩ በተለያዩ ጊዜያት ከሌላው የመንግሥት ሠራተኛ ከፍ ያለ የደመወዝ ስኬልተፈቅዶላቸው የነበሩ 33 ተቋማትም በአሁኑ ማስተካከያ አልተካተቱም። (ዝርዝራቸው ከግርጌ ቀርቧል፡፡)

ስለሆነም ይህ የአሁኑ የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ የሚመለከተው ከተጠቀሱት ውጪ ያሉትንበፌዴራልና በክልል ያሉ በመንግሥት በጀት የሚተዳደሩ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የፖሊስና መከላከያ ሠራዊት አባላት፣የሕዝብ ተመራጮችንና ተሿሚዎችን ነው። ይህም በተሟላ ጥናት ላይ የተመሠረተና የመንግሥትንም የመክፈል አቅምያገናዘበ በመሆኑ ፍትሃዊ ነው።

የአሁን የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ዝቅተኛ ደመወዝ 582 ብር የነበረውን መነሻ ደመወዝ ወደ 860 ስኬሉን ከፍየሚያደርግ እና መድረሻ ጣሪያውን 1,439 ብር የሚያደርግ ነው። ከፍተኛ ደመወዝ ፕሣ – 9 ሲሆን 5,781 ብርየነበረው መነሻው ወደ 7,647 በማሳደግ እና ጣሪያውን 10,946 በማድረግ ስኬሉ ተሻሽሏል።

አሁን የተደረገውን የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ በተመለከተ ያለው ሁኔታ ይህ ሆኖ ሳለ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይየፐብሊክ ሰርቫንቱን የደመወዝ ስኬል ማስተካከያን እንደ ደመወዝ ጭማሪ በመውሰድ በቅርቡ ማስተካከያ የተደረገላቸውንመምህራንንም ይመለከታል በሚል የሚራመደው ሀሳብ የተሳሳተ መሆኑን መረዳትና ትክክለኛውን ሁኔታ መገንዘብያስፈልጋል።

የመምህራን ደመወዝ ስኬል ማስተካከያ በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ሐምሌ 2008 ዓ.ም ላይ ሲደረግ መምህራን የሰውኃይልን የመቅረፅ ትልቅ ተልዕኮ ያላቸው በመሆኑ የተለየ ትኩረት በመስጠት ነው። አሁን ለሌሎች ተቋማት የተደረገውየደመወዝ ስኬል ማስተካከያም ቢሆን ከመምህራን የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ልዩነት ያለው ነው።ይህንንም የተወሰኑ አብነቶችን በማንሳት ማየት ይቻላል፡፡

1) መሰናዶ ት/ቤት 2ኛ ድግሪ ያለው ጀማሪ መምህር 4,269 ብር ሲሆን 2ኛ ዲግሪ ያለው ጀማሪ ሠራተኛ በሌሎችተቋማት 3,137 ብር ነው። ይህ ሰባት ዕርከን ልዩነት ያለው ነው። እንዲሁም ከፍተኛ መሪ ርዕሰ መምህር 12,112ብር የሚከፈለው ሲሆን በሌሎች መንግሥት ተቋማት ያለው መካከለኛ አመራር [ዳይሬክተር፣ ሥራ ሂደት ባለቤት፣ ጽህፈትቤት ኃላፊ ወዘተ] 7,647 ብር ይከፈለዋል። ይህ ከአሥር እርከን በላይ ልዩነት ነው።

2) በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመጀመሪያ ዲግሪ በመምህርነት የተቀጠረ 4,662 ብር በሌሎች የመንግሥት ተቋማት2,748 ብር ይከፈለዋል። ይህ የ12 (አሥራ ሁለት) እርከን ልዩነት ያለው ነው። በዚሁ መስክ ከፍተኛ መሪ መምህርIII 11,720 ሲከፈለው በመንግሥት ተቋማት ያለ መካከለኛ አመራር [ዳይሬክተር፣ ሥራ ሂደት ባለቤት፣ ጽህፈት ቤትኃላፊ ወዘተ] 7,647 ብር ይከፈለዋል። ይህ ደግሞ ከአሥር እርከን በላይ ነው።

3) በመጀመሪያ ዲግሪ ቴክኒካል ድሮዊንግ መምህር 4,085 ብር ሲከፈለው በሌሎች ተቋማት ያለው ግን 2,748 ብርይከፈለዋል። ይህ ደግሞ የዘጠኝ እርከን ልዩነት ያለው ነው። በተመሳሳይ ዘርፍ ከፍተኛ መምህር 10,567 ብር ሲሆንበሌሎች ተቋማት 7,647 ብር ነው። ይህ የዘጠኝ እርከን ልዩነት ነው።

4) ከ9ኛ-10ኛ ክፍል ጀማሪ መምህር 3,137 ብር ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪ በሌሎች ተቋማት ጀማሪ 2,748 ብር ነው።ይህም የሦስት እርከን ልዩነት ያለው ነው። የከፍተኛ መሪ መምህር 8,539 ሲሆን በሌሎች ተቋማት መካከለኛ አመራር[ዳይሬክተር፣ ሥራ ሂደት ባለቤት፣ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወዘተ] ደመወዝ ግን 7,647 ነው።

5) ከ1ኛ-8ኛ ክፍል ጀማሪ የዲፕሎማ መምህር 2,404 ብር ሲሆን በሌሎች ተቋማት 2,100 ብር ነው። ይህም የሦስትእርከን ልዩነት ያለው ነው።

6) የሰርተፍኬት መምህራን ጀማሪ መምህር 1,828 ብር ሲሆን በሌሎች ተቋማት 1,370 ብር ነው። ይህ የስድስት እርከንልዩነት ያለው ነው።

ስለሆነም በአጠቃላይ ሲታይ መንግሥት ለመምህራን የተለየ ትኩረት እንደሰጠና ይህም ተገቢ መሆኑን ማየት ይቻላል። በቀጣይነትም በተለይ የመኖሪያ ቤት፣ የትራንስፖርትና መሰል ድጋፎች በሁሉም አካባቢዎች አቅም በፈቀደ መጠን ደረጃ በደረጃ እየተሟሉ መሄድ ይኖርባቸዋል። ከዚህ አኳያ የተጀመሩ ሥራዎችም አበረታች ናቸው። በዚህ አጋጣሚ መላ መምህራን እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት የምታደርጉትን ትጋት በማጠናከር በሀገራችን የሕዳሴ ጉዞ ላይ አሻራችሁን ለማሳረፍ እንድትረባረቡ ጥሪ እናቀርባለን።

በተለያዩ ጊዜያት ከሌላው የመንግሥት ሠራተኛ ከፍ ያለ የደመወዝ ስኬል ተፈቅዶላቸው የነበሩ

1. የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት ተመራማሪዎች

2. ብሔራዊ ኘላን ኮሚሽን

3. የፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል

4. የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን

5. የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር

6. ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር

7. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

8. የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት

9. የብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዮት የተመራማሪዎች

10. ብሔራዊ የአፈር ምርምር ላቦራቶሪ

11. ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ምርምር ማዕከል ተመራማሪዎች

12. የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን

13. የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር

14. የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን

15. የደን ምርምር ኢንስቲትዮት

16. የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዮት

17. የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር

18. የቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለስልጣን

19. የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ የማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዮት

20. የከተሞች የሥራ እድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ

21. የታላቁ የኢትጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት

22. ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዮት

23. ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

24. ከፍተኛ ፍርድ ቤት

25. የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

26. የተቀናጀ መሠረተ ልማት ማስተባበሪያ ኤጀንሲ

27. የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂያዊ ጥናት ኢንስቲትዮት

28. የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

29. የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኘሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዮት

30. የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ

31. የኢትዮጵያ ኘሬስ ድርጅት

32. የፋይናንስ ደህንንት መረጃ ማዕከል

33. ብሔራዊ መረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ

 

ምንጭ፦ http://eprdfblog.blogspot.ca/

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy