Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ቻይና ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች

0 390

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ቻይና ከአፍሪካ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ዛሬ አስታወቀች።የቻይና ህዝቦች ፖለቲካዊ ምክክር ብሄራዊ ኮሚቴ በዓመቱ የመጀመሪያው ጉባዔውን ባካሄደበት ወቅት እንደተገለጸው፤ በዚህ ዓመትም ቻይና ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች።በጉባዔው ፕሬዚዳንት ሺ ጂፒንግን ጨምሮ ከመላ አገሪቷ የተወከሉ ከሁለት ሺ በላይ የኮሚቴው አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።ጉባዔው በመክፈቻው በብሔራዊ ኮሚቴው ሊቀ_መንበር ዩ ዤንግሼንግ የቀረበውን ያለፈው ዓመት አገራዊ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርትና ቀጣይ ዕቅድን አድምጧል።በአገራዊ ዕቅዱ ቻይና ከአፍሪካ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ትብብር በዚህ ዓመትም አጠናክራ እንደምትቀጥል ይፋ ሆኗል።አፍሪካ የጤና ዘርፏን እንድታዘመንና ተደራሽነቱን ማስፋት እንድትችል የቻይና ድጋፍ ቀጣይነት ይኖረዋል።በተለይ ቻይና ገቢራዊ ማድረግ በጀመረችው በ “ዋን ቤልት ኤንድ ሮድ” ኢኒሼቲቭ አማካኝነት አፍሪካን በመሰረተ ልማት ለማስተሳሰር እንደምትሰራ አረጋግጣለች።የአፍሪካ ቻይና ወዳጅነት ለማጠናከርም በኢኒሼቲቩ ማዕቀፍ ሥር የህዝብ ለህዝብና ባህላዊ ትስስር እንዲጎለብት እንደሚደረግም ነው የተገለጸው።ቻይና ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላትን ፈርጀ ብዙ ትብብር ወደላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገርም ጥረት እንደሚደረግ ተመልክቷል።ኢኒሼቲቩ ቻይና ከእስያ፣ ከአፍሪካና ከአውሮፓ አገሮች የጥንቱን የየብስና የባህር የንግድ መስመርን ተከትሎ በመሰረተ ልማትና በንግድ ማቆራኘትን ዓላማ ያደረገ ነው።ባለፈው ዓመት ቻይና በአፍሪካ ያደረገችው ቀጥተኛ የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ከሦስት  ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ መድረሱ የአገሪቷ የንግድ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።ጉባዔው በቀጣይ ሁለት ቀናት በ13ኛው አገራዊ የአምስት ዓመት ዕቅድና በሌሎች ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መዋቅራዊ ለውጦች ዙሪያ እንደሚመክር ይጠበቃል።በዚህም ቻይና ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላትን የንግድ የኢንቨስትመንት ግንኙነት ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልበት ዙሪያ እንደሚነጋገር ነው የተገለጸው። የምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ዋንግ ጉ ኪንግ ጉባዔውን አስመልክተው ትናንት ለውጭና ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች እንደገለጹት፤ ቻይና ባለፈው ዓመት ለዓለም ኢኮኖሚ መጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጋለች።አገሪቷ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በ “ዋን ቤልት ኤንድ ሮድ” ኢኒሼቲቭ ማዕቀፍ በ 53 አገሮች ያደረገችው ኢንቨስትመንት 14 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን በማሳያነት አንስተዋል።ቻይና እና ኢትዮጵያን ጨምሮ እንደ ኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያ፣ አንጎላ፣ ናይጄሪያና ሌሎች የአፍሪካ አገሮች የመሰረተ ልማት አውታራቸውን እንዲያስፋፉ እገዛ እያደረገች መሆኗን የሚገልጹት ደግሞ በቤጄንግ የሬንሚን ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ዋንግ ዪዊ  ናቸው።ባለፈው ዓመት በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ በተካሄደው የአፍሪካ – ቻይና ትብብር ፎረም ላይ ቻይና ባለ አሥር ነጥብ የትብብር ዕቅድ አቅርባ ለአሕጉሪቷ 60 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመስጠት መወሰኗን ጠቅሰዋል።“ቻይና የአፍሪካ ግዙፍ የልማት አጋር ናት” የሚሉት ፕሮፌሰሩ፤ ከአሕጉሪቷ አገሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ለደቡብ ደቡብ ትብብር ማሳያ ተደርጎ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።ኢትዮጵያና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1970 በይፋ መጀመራቸው መረጃዎች ያሳያሉ።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy