ቻይና እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2017 አጠቃላይ ሀገራዊ እድገት እቅድ ወደ 6 ነጥብ 5 ዝቅ መደረጉን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊኪ ኪያንግ አስታወቁ።ሀገሪቱ በተያዘው ዓመት 6 ነጥብ 5 በመቶ አጠቃላይ ሀገራዊ እድገት ለማስመዝገብ ያቀደች ሲሆን፥ አምና በተመሳሳይ ካስቀመጠችው ከ6 ነጥብ 5 እስከ 7 በመቶ የቀነሰ ነው ተብሏል።የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊኪ ኪያንግ ዛሬ በሀገሪቱ ፓርላማ ቀርበው የሀገሪቱን የስራ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህን ያስታወቁት።ቻይና በፈረንጆቹ 2016 6 ነጥብ 7 በመቶ አጠቃላይ ሀገራዊ እድገት ያስመዘገበች ሲሆን፥ ከፍተኛ የባንክ ብድር የተመዘገበበት፣ የቤት ልማት በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረበት እና በመንግስት ኢንቨስትመንት ላይ በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ የፈሰሰበት እንደነበረ ተነግሯል።እንዲሁም በከተማ ለ13 ነጥብ 14 ሚሊየን ሰዎች አዳዲስ የስራ እድል መፍጠሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።ሆኖም ግን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በተጠናቀቀው 2016 የቻይና ኢኮኖሚ በ26 ዓመት ውስጥ ፍጥነቱ በጣም የቀነሰበት እንደነበር ተነግሯል።ሀገሪቱ አሁን ላይ ያቀደቸው አጠቃላይ ሀገራዊ እድገት ጤናማ የሚባል ነው የተባለ ሲሆን፥ ከኢኮኖሚ እድገት በላይ ግን የተለያዩ ማሻሻያዎችን እንደምታደርግ ይጠበቃል ተብሏል። ምንጭ፦ www.reuters.com
- Comments
- Facebook Comments
Follow Us @ethiopiaprosperous
porn videos