Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አለማቀፉ የአልጄሪያ ሲቪታል ግሩፕ ኩባንያ በኢትዮጵያ ሶስት ፋብሪካዎች ለመገንባት እንደሚፈልግ አስታወቀ

0 710

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አለም አቀፉ የአልጄሪያ ሲቪታል ግሩፕ ኩባንያ ዘይት፣ ስኳርና የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ሶስት ፋብሪካዎችን በኢትዮጵያ መገንባት እንደሚፈልግ ገለፀ።ይህን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያግዘውን የመግባቢያ ስምምነት ከመንግስት የልማት ድርጅት ሚኒስቴር ጋር ተፈራርሟል።ሲቪታል የሚገነባው የዘይት ፋብሪካ በዓመት 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ዘይት በማምረት ለሃገር ውስጥና ለውጭ ማቅረብ የሚያስችል ነው።በጥሬው ወደ ውጭ የሚላኩ የቅባት እህሎችን እሴት በመጨመር ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንደሚያስገኝ ተነግሯል።ሪፋይንድ ሹገር ወይም የተጣራ ስኳር የሚያመርተው ፋብሪካ ደግሞ 1 ሚሊዮን ቶን ኩንታል የተጣራ ስኳር ለማምረት አስቧል ።በስምምነቱ ወቅት የመንግስት ልማት ድርጅት ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ እንዳሉት፤ኩባኒያው በኢትዮጵያ በሶስት መስኮች ያሳየው የቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍላጎት ሌሎች አለም አቀፍ ኩባኒያዎችን ለመሳብ ያግዛል። ሲቪታል በመስኩ ያዳበረው እውቀትና ቴክኖሎጂም ሃገሪቱ የያዘቻቸውን ፕሮጀክቶች በማሸጋገር ለመጠቀም ያስችላል ብለዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy