Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አሜሪካ ለሶማሊያ ልዩ ወታደራዊ ኃይሎችን እስከ መላክ የዘለቀ ድጋፍ የማድረግ ውጥን እንዳላት ተነገረ

0 964

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ሽብረተኛው ቡድን አይ ኤስ በሶማሊያ እየተሰፋፋ መሄዱን ተከትሎ ወታደራዊ ዘመቻ የሚያካሄዱ ልዩ ኃይሎች የመላክ ወጥን እንዳለው ተሰማ፡፡በሶማሊያ በአጥፍቶ ጠፊዎች በሀገሪቱ ሆቴሎች እና ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ሽብርተኛው ቡድን አልሸባብ በተደጋጋሚ ጥቃቶችን እያደረሰ ይገኛል፡፡ታጣቂው ቡድን ከአይ ኤስ ጋር በፈጠረው ግንኙነት በሀገሪቱ ቡድኑ የሚያካሂዳቸው ጥቃቶች በርክተዋል፡፡ዩናይትድ ስቴትስ ይህንኑ ጽንፈኛ ቡድን ለመደምሰስ በሰው አልባ አውሮፕላኖች የምታካሂዳቸውን ድብደባዎች ጎን ለጎን ወታደራዊ ዘመቻዋን ለማስፋት እቅድ እንዳላት አልጀዚራ ዘግቧል፡፡የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ለዋይት ሃውስ ከላካቸው ምክረ-ሃሳቦች አንዱ አሜሪካ ልዩ ወታደራዊ ኃይሎች ወደ ሶማሊያ በመላክ የሶማሊያን ብሄራዊ ጦር እንዲያግዙ የሚጠይቅ ነው፡፡ልዩ ኃይሎቹ በሶማሊያ እንዲሰማሩ ማድረግ ቀልጣፋ ቅድመ መከላከል እርምጃዎችን ለመውሰድም የሚያስችል መሆኑ እንደምክንያት ተጠቅሷል፡፡ዩናይትድ ስቴትስ በሶማሊያ 14 ጊዜ በሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃቶችን ያካሄደች ሲሆን፥ ሀሰን አሊ ዳሂርና አብዱላሂ ሀጂ ዳውድን ጨምሮ የአልሸባብ ከፍተኛ መሪዎችን መግደል ችላለች፡፡እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2007 ጀምሮ በሶማሊያ የሰፈረው 22 ሺህ የአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ ጦር አማካኝነት በአልሸባብ ላይ ድልን መቀዳጀት ቢቻልም፥የህብረቱ ጦር በ2020 በዋናነት በበጀት ምክንያት ሀገሪቱን ለቆ ለመወጣት ወጥን እንዳለው ይነገራል፡፡አልሸባብ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በሞቃዲሾ ሚያካሂዳቸው ጥቃቶች እየጨመሩ መምጣታቸው የአዲሱ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ መሀመድ በሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን የመገንባት ጥረታቸውን ስጋት ውስጥ መክተቱ እየተነገረ ነው፡፡ከአይ ኤስ ጋር ቁርኝት ያላቸው ተዋጊዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሶማሊያ እየበረከቱ መሄዳቸው ለዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ዘመቻ ፈታኝ ይሆናሉ ተብሏል፡፡እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2015 ጀምሮ ከሽብርተኛው አልሸባብ የወጡ ታጣቂ አንጃዎች ለአይ ኤስ አጋርነታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ምንጭ፦አልጀዚራ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy