Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አርታሌ እሳተ ገሞራ የናሳን ቀልብ ስቧል

0 1,008

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአሜሪካው የጠፈር መርምር ተቋም/ ናሳ/ የሰዎች እግዛ ሳይፈልግ በሰው ሰራሽ የኮምፒውተር የማሰብ አቅም በመጠቀም በኢትዮጵያ የሚገኘውን አርታሌ የእሳተ ገሞራ እንቅስቀሴን የሚያሳይ ፎቶ ማንሳቱን ይፋ አድርጓል፡፡

ፎቶው የተነሳውም ሰው ሰራሽ የኮምፒውተር ቴክኖሎጂው/ Artificial intelligence/ ሰዎች ትዕዛዝ ሳይሰጡት መረጃው እንደሚያስፈልግ ቀድሞ በመረዳት በመሬት ዛቢያ የሚሽከረከሩ ሳተላይቶችን ምስሉን እንዲሰበስቡ ትዕዛዝ ከሰጠ በሃላ ነው ተብሏል፡፡

በሙከራ ደረጃ ባለው በዚህ ቴክኖሎጂ በእሳተ ገሞራ ላይ ምርምር ለሚያደርጉ ባለሞያዎች ጠቃሚ መረጃ እንደሰጣቸው ነው የተነገረው፡፡ተመራማሪዎቹ ናሳ በጠፈር ሳተላይቶቹ አማካኝነት የእሳተ ገሞራ እንቅስቃሴን በተመለከተ መረጃ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ቴክኖሎጂው ግን ይህ ጥያቄ ከመነሳቱ በፊት ቀድሞ ከሌሎች ሳተላይቶች ጥቆማ ደርሶት ስለነበር ፎቶው በሌሎች ሳተላይቶች እንዲነሳ አድርጓል ተብሏል፡፡

በዚህም የእሳተ ገሞራው ቅልጥ ድንጋይ ሐይቆችና ጭሶች በፎቶው ምስል ላይ እንዳለ ለማየት ተችሏል፡፡ላለፉት 12 ዓመታት ይህ ሰው ሰራሽ የኮምፒውተር ቴክሎኖጂ በስሩ የሚገኙ ሳተላይቶችን በመምራት ከጠፈር ምድር ላይ የሚከወኑ ጠቃሚ መረጃዎችን ለተመራማሪዎች  በመሰብሰብ ያቀብላል፡፡

ቴክኖሎጂ ከጠፈር ምድር ላይ ተፈላጊ መረጃ ሲያገኝ በ90 ደቂቃ ውስጥ ለተመራማሪዎች ሲጠቁም፤ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ደግሞ በመሬት ለሚዞሩ ሳተላይቶች መረጃውን እንዲሰበስብ ትዕዛዝ የማስተላለፍ አቅም እንዳለው ተነግሯል፡፡

የሙከራው ቴክኖሎጂ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ዓመት ስራውን እንደሚያቆም ተጠቅሷል፡፡በቀጣይ ቴክኖሎው የጠፈር መንኮራኩሮችን ተልዕኮ ለማሳካት እገዛ እንዲሰጥ ጥረት ይደረጋል ነው የተባለው፡፡  ምንጭ፦ኢንጋጄት

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy