Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አስተዳደሩ ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለሟቋቋም ውይይት እያደረገ ነው

0 275

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቆሼ አካባቢ በቆሻሻ መደርመስ ምክንያት ጉዳት  የደረሰባቸውን ቤተሰቦች በዘላቂነት ለሟቋቋም ከተጎጂ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያደረገ  መሆኑን አስታወቀ ።

በከተማው አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ለዋልታ እንደገለጹት በቆሼ የቆሻሻ መደርመስ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ቤተሰቦችን በዘላቂነት በማቋቋም ወደ ቋሚ ኑሯቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ።

በአደጋው የጎዱ ቤተሰቦችን የመለየትሥራ እየተከናወነ መሆኑን የጠቆሙት ወይዘሮ ዳግማዊት  በመልሶ  ማቋቋም ሥራዎች ዙሪያ ከተጎጂ  ወገኖች ተወካዮች ጋር የጋራ መግባባት ከተደረሰ በኋላ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር ተናግረዋል ።

እስካሁን ድረስ ለአደጋው ተጎጂ ወገኖች 76 ሚሊዮን ብር የድጋፍ ገንዝብ መሠጠቱንና ቃል መገባቱን የሚገልጹት ወይዘሮ ዳግማዊት 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ቁሳቁስና የምግብ እርዳታ ድጋፍ ለተጎጂዎች ተበርክቷል ብለዋል ።

በቆሼ አካባቢ አደጋ  ተጋለጭ የሆኑ ነዋሪዎች አደጋ  እንዳይጋለጡ ለማድረግ  በአንድ ቦታ በማሰባሰብ  የዕለት  ደራሽ እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ወይዘሮ ዳግማዊት ገልጸዋል ።

በቆሼ አካባቢ በቆሻሻ መደርመስ ምክንያት አደጋ ምክንያት 113 ህይወታቸውን ያጡ መሆኑ  ይታወቃል ።

በአደጋው ለደረሰባቸው  ወገኖችን ለመደገፍ  በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  በተከፈተው የሂሳብ ቁጥርና  በሞባይል አጭር ጽሑፍ መላኪያ ቁጥር የተለያዩ የህብረተሰብ  ክፍሎች ድጋፎቸውን እያደረጉ ነው ።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy