Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አየር መንገዱ ሶስት አዳዲስ በረራዎችን ነገ ይጀምራል

0 914

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኦስሎ፣ ቪክቶሪያ ፏፏቴና አንታናናሪቮ ከተሞች የሚያደርገው አዳዲስ በረራ ነገ ይጀምራል።አየር መንገዱ ወደ ኖርዌይ መዲና አስሎ፣ የዚምባብዌ የቱሪስት መዳረሻ ወደ ሆነው ቪክቶሪያ ፏፏቴ እና የማዳጋስካር ዋና ከተማ አንታናናሪቮ ከነገ እሁድ ጀምሮ አዲስ በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም አዳዲስ የሚጀመሩትን በረራዎች አስመልከተው እንዳሉት፥ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ2025 አየር መንገዱ አለም አቀፍ መዳረሻዎቹን 120 ለማድረስ የያዘውን እቅድ ቀድሞ ሊያሳካ ይችላል።አየር መንገዱ በአፍሪካውያን ሙሉ በሙሉ የሚመራ መሆኑ ለኢትዮጵያውያን እና ለአፍሪካውያን ኩራት መሆኑንም ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር በረራው ወደ ሰሜን አውሮፓ ኦስሎ መጀመሩ አዲስ ግንኙነት፤ አዲስ የገበያና የኢንቨስትመንት እድሎችን ከመፍጠሩ ባሻገር ለሃገራቱ የሁለትዮሽና አለም አቀፋዊ ግንኙነትን ያሳድጋል ብለዋል።

ከነገ ጀምሮ በየሳምንቱ አንድ ቀን የሚደረገው ቀጥታ አዲስ አበባ- ኦስሎ በረራ አፍሪካን ከሰሜን አውሮፓ ጋር በማስተሳሰር ብቸኛ አየር መንገድ እንደሚያደርገውም ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የማዳጋስካር ኤምባሲ አማካሪ ሚስ ኒሪና አንጀላ በበኩላቸው፥ ከአዲስ አበባ- ወደ አንታናናሪቮ የሚደረገው በረራ የሁለቱን ሃገራት የንግድና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከማሳደጉም በላይ በአጀንዳ 2063 አፍሪካን ለማስተሳሰር ለተያዘው ራዕይ እውን መሆን ማሳያ ነው ብለዋል።

አየር መንገዱ በአፍሪካ ሃገራት በሚያደርጋቸው በረራዎች አህጉሪቷን በኢኮኖሚ፣ ንግድና ቱሪዝም ልማት ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል ሚስ ኒሪና።

በመጭዎቹ 4 ወራት ውስጥ የእስያ መዳረሻዎቹን ለማስፋት ሲንጋፖር፣ የኢንዶኔዥያ መዲና ወደ ሆነችው ጃካርታና የቻይናዋ የጥንት ከተማ ቼንግዱ አዲስ በረራ እንደሚጀምር ገልጿል።

አፍሪካን ከቀሪው ዓለም ጋር የሚያስተሳስረው የኢትዮያ አየር መንገድ በሳምንት 28 በረራዎችን ወደ ቻይና ፣20 በረራዎችን ወደ አሜሪካ እና 54 በረራዎችን ደግሞ ወደ አውሮፓ ከተሞች እንደሚያደርግ የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy