Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አገሪቱ የምታቀርበው የኢንቨስትመንት ማበረታቻ የደቡብ አፍሪካውያን ባለሃብቶችን ቀልብ ስቧል

0 523

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ ለውጭ ባለኃብቶች የምታቀርበው የኢንቨስትመንት ማበረታቻና የሕግ ከለላ በዘርፉ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳሳደረባቸው ከደቡብ አፍሪካ የመጡ ባለሃብቶች ተናገሩ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከደቡብ አፍሪካ የኢንቨስትመንት ልዑካን ቡድኖች ጋር በኢትዮጵያ መዋዕለ-ነዋያቸውን ማፍሰስ በሚችሉበት ሁኔታ ዙሪያ ምክክር አድርጓል።በውይይቱ ወቅት ለባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭና በመንግሥት ለውጭ ባለሃብቶች ስለሚቀርቡ ሕጋዊ ከለላዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።ኢትዮጵያ ለውጭ ባለኃብቶች የምታቀርበው የኢንቨስትመንት ማበረታቻና ጥበቃ አስተማማኝ በመሆኑ በዘርፉ ለመሰማራት እንደሚፈልጉ ነው ባለሃብቶቹ የገለጹት። የተለያዩ ምርቶችን ለውጭ ገበያ ማቅረብ ላይ የተሰማሩት ሳንዲሌ ንድሎቩ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት የመሰማራት ፍላጎት ነበረን ብለዋል። ይህም የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ባለኃብቶች ወደ አገሪቱ እንዲመጡ ስለሚፈልግና በአገሪቱም በርካታ የገበያ ዕድል መኖሩን በምክንያትነት ጠቅሰዋል።የአገሪቱ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥም በምስራቅ አፍሪካ ያለውን ገበያ ለመጠቅም እንደሚያስችልና በመንግሥት የሚቀርበው ማበረታቻም ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ፍላጎት ያሳድራል ብለዋል።በግብርና ምርቶች ላይ የተሰማራችው ኤልሳቤ ፍርይ በበኩሏ በዛሬው ዕለት በአገሪቱ በመስኩ ለመሰማራት የምንፈልጋቸውን ዋና ጉዳዮች በዝርዝር ገለጻ ሲደረግ ለማግኘት ችለናል ብለዋል። በቀጣይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ስምምነት እንደሚፈጽሙ ገልጸው በአገሪቱ ምቹ ሁኔታ መኖሩን ነው የተናገሩት።   ”በእንስሳትና በእንስሳት ውጤቶች ላይ ለሚሰመራ የውጭ ባለሃብት የአገሪቱ በር ክፍት ነው” ያሉት ደግሞ ሌላው በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩ ባለሃብት አዴሌ ፋዉል ናቸው።በአገሪቱ በዘርፉ አምርቶ ምርቶችን ወደ ጎረቤት አገራት ለመላክም ዕድል መኖሩንና የሚቀርቡት ማበረታቻዎችም በተመሳሳይ ለመሥራት ምቹ መደላድል እንደሚፈጥሩ ነው ያስረዱት። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቢዝነስ ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሔር በበኩላቸው የውጭ ባለሃብቶች ከአፍሪካ አገራትም ጭምር ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።ይህንም ለማድረግ በተለይም በአገሪቱ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች የመለየትና የማስተዋወቅ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተዋል።  ”በደቡበ አፍሪካ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲም ባለኃብቶቹ ወደ ዚህ እንዲመጡ አድርጓል” ያሉት ዳይሬክተሩ ይህም በቀጣይ እንደሚጠናከር ነው ያረጋገጡት።በኢትዮጵያና በደቡበ አፍሪካ ባለኃብቶች መካከል የተደረገው ይህ ስብሰባ ለአራተኛ ጊዜ ሲሆን በውይይቱ ላይ ከ20 በላይ የደቡብ አፍሪካ ባለሃብቶች ተሳታፊ ነበሩ።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy