Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ ከቡና ምርት የሚገባትን ያህል ተጠቃሚ አለመሆኗ ተገለፀ

0 676

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልከው የቡና ምርት የሚገባትን ያህል ጥቅም እያገኘች አለመሆኑን ዘ ጆርናል የተሰኘው ድረ-ገፅ አስነብቧል፡፡ቡናን ጨምሮ በግብርና ምርቶች ላይ እሴት ሳይጨምሩ መላክ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚገኙ የንግድ ተቋማት በራሳቸው ብራንድ እሴት በመጨመር ከትርፉ ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡እንደ ዘ ጆርናል ድረ ገጽ ዘገባ ኢትዮጵያውያን በቡና ምርት ላይ እሴት በመጨመርና የቡና ኢንዱስትሪን በማስፋፋት ከድህነት መላቀቅ እንደሚያስችላት ገልጿል፡ድረ-ገፁ የፈረንሳይ የወይን መጠጥ ኢንዱስትሪን እንደ አብነት በመውሰድ ፈረንሳይ የምታመርተውን የወይን ፍሬ ወደ ወይን መጠጥነት በመቀየርና በጠርሙስ አሽጋ ለአለም ገበያ በማቅረቧ ከኢንዱስትሪው በየአመቱ 12 ቢሊዮን ዩሮ ታገኛለች፡፡ይህም ገቢዋ በአገሪቱ ውስጥ የስራ እድልን በመፍጠር የምታገኘውን ትርፍ በአገሪቱ ልማት ላይ ለማዋል እንዳስቻላት የዘ ጆርናል ዘገባ ያስረዳል፡፡በዚሁ መልኩ ከወይን እና ከቢራ መጠጦች በላይ ተወዳጅ የሆነውን ቡና በማምረት ከሚታወቁት አገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ከቡና ምርት በአመት 760 ሚሊዮን ዩሮ ብቻ እንደምታገኝ ገልጿል፡፡ ድረ-ገፁ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የትርፍ ልዩነት በማነፃፀር ችግሩ የቱጋ እንደተፈጠረ ያብራራል፡፡ ፍትሃዊ የንግድ ልውውጥ ያለመኖሩን ነው በዋና ምክንያትነት ያስቀምጣል፡፡በዓለም ላይ በቀን ከ2 ቢሊዮን ሲኒ በላይ ቡና ይጠጣል፡፡ ይህም በአለም ገበያ ዓመታዊ የቡናን ዋጋ ከ100 ቢሊዮን ዩሮ በላይ ያደርገዋል፡፡በማደግ ላይ ባሉ አገራት 100 ሚሊዮን የሚጠጋ ቁጥር ያላቸው በድህነት ላይ የሚገኙ ዜጎች በቡና ላይ የተመሰረተ ህይወት ይገፋሉ፡፡ኢትዮጵያ የቡና የመጀመሪያዋ መገኛ የአረቢካ ቡና ባለቤተና የሀረር፣ ሲዳሞና የይርጋጨፌ ተፈጥሮአዊ የጫካ ቡና ብራንዶች ባለቤት ነች፡፡ምንጭ፡- ዘ ጆርናል

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy