የአለም ባንክ በኦሮሚያ ክልል ለተመረጡ የደን ልማትና የመሬት አስተዳደር ፕሮጀክቶች የሚውል የ18 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚንስቴር በኩል አደረገ፡፡
ባንኩ ዛሬ ያደረገው ድጋፍ ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ መርሃ ግብር ማስተግበሪያ በኦሮሚያ ክልል ለተመረጡ የደን ልማት ፕሮጀክቶች ከሚዉለው የ68 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አካል መሆኑም ታውቋል ፡፡
መርሀ ግብሩ በአካባቢው ማህበረሰብ ሊከናወኑ የሚችሉ እንደ የደን ቱሪዝም የመሳሳሉ ከአካባቢ ጋር ተስማሚነት ያላቸውን ስራዎቸ ለማስፋፋት እንደሚውልም ተገልጿል፡፡
ከኢትዮጵያ በኩል በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚንስቴር ሚንስትር ድኤታ አቶ አድማሱ ነበበ ከአለም ባንክ የአዲስ አበባ ተወካይ ካሎሬን ቱርክ ድጋፉን ተረክበዋል፡፡
ሪፖርተር፡- ሙሉጌታ ተስፋዬ