Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ የእስያ መሰረተልማት ኢንቨስትመንት ባንክ አባል ሆነች

0 431

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ በቻይና መንግስት የሚደገፈው የእስያ መሰረተልማት ኢንቨስትመንት ባንክ አባል መሆኗን ባንኩ ገለጸ።ባንኩ ኢትዮጵያን ጨምሮ 13 አዳዲስ አባላትን የተቀበለ ሲሆን፥ 13 አዳዲስ የባንኩ አባላት ሲጨመሩ የባንኩ አባል ሀገራት ወደ 70 አድጓል።

ባንኩ ከተመሰረተ ወዲህ አዳዲስ አባላትን ሲቀበል ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑንም ነው በድረገጹ የገለጸው፡፡የእስያ መሰረተልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ከእስያ ውጪ ስምንት አባል ሀገራትን ያካተተ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ፣ ካናዳ፣ ቤልጂየም፣ ሃንጋሪ፣ አየርላንድ፣ ፔሩ፣ ሱዳን ሪፐብሊክ እና ቬኒዝዌላ ናቸው፡፡

አምስቱ የቀጠናው አባላት ደግሞ ሆንግ ኮንግ፣ አፍጋኒስታን፣ አርሜኒያ፣ ፊጂ እና ቲሞር ሌስት መሆናቸው ተነግሯል፡፡ይህ የፋይናንስ ተቋም በምዕራቡ አለም የሚደገፈው የአለም ባንክ እና የእስያ ልማት ባንክ ተፎካካሪ በመሆኑ ከጅምሩ ዩናይትድ ስቴትስ አትደግፈውም ነበር፡፡

አሁን ግን የአሜሪካ ወዳጅ ሀገራት እንደ ብሪታኒያ፣ ካናዳ፣ ጀርመን፣ አውስትራሊያ እና ደቡብ ኮሪያን እየሳበ መምጣቱ ተጠቁሟል፡፡የባንኩ ፕሬዚዳንት ጂን ሊ ኪን ከመላው አህጉር አባላትን መሳቡ እንዳኮራቸው ጠቅሰው፥ ተጨማሪ አባላት ወደፊት እንደሚኖሩ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦ ሬውተርስ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy