Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢጋድ አስቸኳይ ስብሰባውን በኬንያ እያካሄደ ነው

0 439

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አስቸኳይ ስብሰባውን በኬንያ እያካሄደ ነው።በኬንያ መዲና ናይሮቢ እየተካሄደ ያለው ስብሰባ፥ በሶማሊያ ስደተኞች ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በመምከር ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ያለ ነው ተብሏል።በስብሰባው ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ፥ የኢጋድ አባል ሃገራት መሪዎችና ተሳታፊዎች ታድመዋል።

ከየመን፣ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር የሚገኙ ተቋማትና ከአለም አቀፍ የባንክ ተቋማት የተውጣጡ ተወካዮችም ይገኛሉ። መሪዎቹ በተለያዩ ሃገራት ለሚገኙ ሶማሊያውያን ስደተኞች ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት በሚያስችሉ ሃሳቦች ላይ እየተወያዩ ነው።

አሁን ላይ በሃገሪቱ እየታየ ያለውን ሰላምና ጸጥታ በመጠቀም፥ ለሃገሬው ዜጎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይም እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

በስብሰባው ላይ አዲሱ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሶማሊያውያን ስድተኞችን ተቀብለው እያስተናገዱ ላሉ ሃገራት በመንግስታቸው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በበኩሉ፥ አሁን ያለው የስደተኞች ሁኔታ አስቸኳይ መፍትሄ ሊበጅለት እንደሚገባ ገልጿል።ከዚህ ባለፈም ወደ ሃገራቸው ለሚለሱ ሶማሊያውያን ምቹ እና አስተማማኝ ሁኔታን መፍጠር እንደሚገባም ነው የገለጸው።

haile_uhuru.jpg

በተያያዘም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር መምከራቸው ታውቋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy