Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

እንግሊዝ በተለያዩ የልማት ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደምትፈልግ ገለጸች

0 342

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

እንግሊዝ በተለያዩ የልማት ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደምትፈልግ የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ገለጹ።ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የእንግሊዙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ እንግሊዝ ሃገሪቱ በልማትና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የምታደርገውን እንቅስቃሴ በመደገፍ በጋራ መስራት ትፈልጋለች።

ሃገሪቱ የምታከናውናቸውን የልማት ተግባራት በመደገፍ የእንግሊዝ ባለኃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ለማድረግ ከመንግስት ባለፈ በግላቸው ጥረት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው፥ ሁለቱ ሃገራት ግንኙነታቸውን በማጠናከር የእንግሊዝ ባለኃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ቢያፈሱ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ገልጸዋል።በውይይታቸውም የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ውጤታማ ማድረግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይም መክረዋል።

እንግሊዝ በሶማሊያና በደቡብ ሱዳን አካባቢ ያለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታትና ሰላም ለማምጣት ኢትዮጵያ ለምታደርገው ጥረት ድጋፏን እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy