Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኦህዴድ ለክልሉ ህዝብ ተጠቃሚነት የገባውን ቃል በተግባር ይፈፅማል- አቶ በከር ሻሌ

0 617

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ለክልሉ ህዝብ ተጠቃሚነት የገባውን ቃል በተግባር እንደሚፈፅም የድርጅቱ ማዕካላዊ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በከር ሻሌ ገለፁ።

እንደሌላው ኢትዮጰያዊ ሁሉ የኦሮሞ ህዝብ ዘመናትን ተሻግሮ የመጣ ብሔራዊ ጭቆና ሰለባ እንደነበር ያነሱት ሃላፊው፥ ድርጅቱ ከ27 ዓመታት በፊት እንዲመሰረት ምክንያት የሆነው፥ በመራር ትግል የኦሮሞ ህዝብን ከጭቆና አገዛዝ ማስጣል እንደሆነ ጠቅሰዋል።

አሁን ላይ የኦሮሞ ህዝብ የህይወት መስዋዕትነት ከፍሎ የጭቆና ቀንበሩን ከጫንቃው አንስቶ፥ ሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች እኩል መብት የተጎናፀፉባት ሀገርን እውን አድርጓል ነው ያሉት አቶ በከር።

ኢህዴድ፥ ባለፉት ዓመታት የኦሮሞን ህዝብ ተጠቃሚነት ያራጋገጡ ተግባራትን የመከወኑን ያህል፥ ከስራ ፈጠራ እስከ አኮኖሚ ተጠቃሚነት ድርስ ያልፈታቸው ችግሮች እንዳሉ ይነሳል።

ድርጅቱ የተመሰረተበትን 27ኛ ዓመት ሲያከብር ባለፉት ዓመታት በኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ መስክ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች በማስቀጠል፣ ጥልቅ ተሃድሶው ውጤታማ እንዲሆን እና ህብረተሰቡ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ይሆናል ነው ያሉት አቶ በከር።

በክልሉ በአሁኑ ወቅት አንጻራዊ መረጋጋት ያለ ሲሆን፥ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ለሁለንተናዊ ለውጥና ተጠቃሚነት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በዓሉ ሲከበር የሰላምና የልማት አጀንዳዎችን በማስፈፀምና የጥልቅ ተሃድሶ መነሻ እና መድረሻ የህዝቡ ተጠቃሚነት መሆኑን በተግባር በማሳየት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ያለውን ሰፊ የተማረ የወጣት ሀይልን የስራ ባለቤት ማድረግ በድርጅቱ የሚመራው የክልሉ መንግስት ቀዳሚ ትክረት መሆኑን የጠቀሱት ሃላፊው፥ ከፌደራል መንግስት ከተሰጠው የወጣቶች ስራ ፈጠራ ተዘዋዋሪ ፈንድ ላይ የራሱን በመጨመር፥ ለወጣቶች ስራ ፈጠራ የሚውሉ አማራጮችን እያቀረበ መሆኑን አንስተዋል።

በክልሉ በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች የሚገኙ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፥ ለዚህም 6 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ተመድቦ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የሙስና እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ መሁኑን የሚገልጹት አቶ በከር፥ በዚህም ኪራይ ሰብሳቢነትን በመታገል መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እየተሰራ ሲሆን፥ በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የገለፁት።

በህዝቡ መካከል የመነጠልና የመከፋፈል ስሜትን ለመፍጠር የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያራምዷቸውን ህዝባዊ ያልሆኑ እኩይ አስተሳሰቦች እያረሙ መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል።

ኦህዴድ ለክልሉ ህዝብ ሁለንተናዊ ለውጥ እና ተጠቃሚነት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ውጤት እንዲያመጣ መላው ህዝብ እና አመራሩ በጋራ ሊሰሩ ገባል ነው ያሉት።

ኦህዴድ የተመሰረተብት 27ኛ የምስረታ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች በተሃድሶ መንፈስ እና ቃልን በማደስ እየተከበረ ይገኛል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy