Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኦባማ በፈረንሳይ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንዲፎካከሩ የድጋፍ ፊርማ እየተሰባሰበ ነው

0 291

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

“Oui on peut!” በፓሪስ ጎዳናዎች ላይ የተለጠፉ ፖስተሮች ላይ የሚነበብ በፈረንሳይኛ የተፃፈ ፅሁፍ ነው፤ “አዎ እንችላለን” የሚል ትርጓሜም አለው።

ከሰሞኑ የ44ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ምስሎች በፓሪስ ተደጋግሞ መታየት የበርካቶችን ቀልብ ስቧል።

ምስሎቹን በመዲናዋ አደባባዮች እና ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች የመስቀሉ ዘመቻ የተጀመረው እንደ ቀልድ ነበር፤ “ባራክ ኦባማ ለምን በቀጣዩን የፈረንሳይ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አይፎካከሩም?” በሚል።

ይህ ዘመቻ በአደባባይ የባራክ ኦባማን ምስል ከመስቀል ተሻግሮ በድረ ገፅ አማካኝነት የድጋፍ ፊርማ ወደማሰባሰብ አድጓል።

በ10 ቀናት ውስጥም ከ45 ሺህ በላይ ሰዎች ኦባማ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ቢፎካከሩ ፍላጎታቸው መሆኑን በመግለፅ ፊርማቸውን አኑረዋል።

የዘመቻው አስተባባሪዎች በመጪዎቹ ስምንት ቀናት 1 ሚሊየን ደጋፊዎችን ለማግኘት አቅደዋል።

obama_france1.jpg

በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳው ወግ አጥባቂው ፍራንኮይስ ፊለን የበላይነቱን መያዛቸው ይታወቃል።

የዚህ ዘመቻ አዘጋጆችም የደበዘዘው የምርጫ ቅስቀሳ በተለያዩ ቀልዶች የተሞላ እንዲሆን ነው ፍላጎታቸው።

ለዚህም “ኦባማ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ለምን አይፎካከርም” የሚል ሀሳብ ከአንድ ጓደኛቸው መነሳቱንና ወደ ተግባር መግባታቸውን ነው ከቀልድ መፍጠሪያ ዘመቻው ከአስተባባሪዎች አንዱ የሆነው አንቶኒዮ ለአሶሼትድ ፕሬስ የተናገረው።

ፖስተሮቹን የለጠፉበት ሂደት ህጋዊ ባለመሆኑም አንቶኒዮ ሙሉ ስሙን ለመጥቀስ አልፈለገም።

አንቶኒዮ የኦባማ ምስል ለታተመባቸው 500 ፖስተሮች፣ ቲሸርቶች እና ኩባያዎች በአጠቃላይ 1 ሺህ 592 የአሜሪካ ዶላር ወጪ ማድረጉን ገልጿል።

ከጓደኞቹ ጋር በከፈቱት ድረ ገፅ አማካኝነትም ቲሸርቶቹን እና ኩባያዎቹን ለሽያጭ ማቅረባቸውን ተናግሯል፤ ምንም እንኳን እስካሁን የተገኘውን ገቢ ባይገልፅም።

ከሽያጩ የተገኘው ትርፍም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የፓሪስ የፖለቲካል ሳይንስ ተቋም ተማሪዎች እንደሚሰጥ ነው አስተባባሪዎቹ የጠቆሙት።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጠጣር ከ1999 ጀምሮ በፈረንሳይ የምትኖረው አሜሪካዊቷ ሳራህ ዋቸር የወጣቶቹን የፊርማ ማሰባሰብ እና ይዘውት የተነሱትን አላማ አድንቃለች።

“ሰዎች ለውጥ ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ቀጥተኛ አይነት ለውጥ ነው የሚፈልጉት። ሁሉንም የሚያሳትፍና ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ሰዋዊ እና ለመላው አለም ክፍት የሆነ ለውጥ ግን ለሁሉም ይበጃል” የምትለው ዋቸር፥ ባራክ ኦባማም ይህን ሁሉ በአሜሪካ አከናውነውታል ብላ እንደምታምን ገልፃለች።

ኦባማ በፈረንሳይ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመወዳደር እድል ወይንም ፍላጎት ባይኖራቸውም የዚህ ዘመቻ አስተባባሪዎች ከሰሞኑ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃንን ቀልብ ስበዋል። FBC

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy