Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከአዲስ አበባ ካርቱም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የፊታችን እሁድ ሊጀመር ነው

0 971

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአዲስ አበባና በካርቱም ከተሞች መካከል የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማስጀመር የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መደረሱን የኢፌዲሪ ፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገልጿል፡፡

በሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች የሚደረገው ድንበር ተሻጋሪ የሆነው  የአዲስ አበባ – ካርቱም የትራንስፖርት አገልግሎት አሁን ለደረሰበት ደረጃ የበቃው ከ8 ዓመታት ውጣ ወረድ መሆኑን በፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የህዝብ አገልግሎትና ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክተሩ አቶ ተስፋዬ በላቸውበተለይ  ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ከባለሥልጣኑ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የመጀመርያው የአውቶብስ ትራንስፖርት አገልግሎት መጋቢት 3 ቀን 2009 ዓ.ም በይፋ ይጀመራል፡፡

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቱ በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንደሚያጠናክር ተመልክቷል፡፡ እንቨስትመንትና ቱሪዝምንም የማጠናከር ዕድል እንዳለው አቶ ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡

በሁለቱ አገራት የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሞ ለረጅም ጊዜ ሲጠና የቆየው የአገራቱ የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት  60 የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ተቆርጦለታል፡፡

ከአዲስ አበባ ካርቱም 1 ሺህ 490 ኪሎ ሜትሮችን የሚሸፍን ሲሆን ህዝብ ትራንስፖርት ሰጪ መኪናዎች አገልግሎቱን ለመስጠት ሁለት ቀናት እንደሚፈጅባቸው ተገልጿል፡፡

ተመሳሳይ አገልግሎት በሌሎች ጎረቤት አገራትም ለመስጠት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ከባለ ስልጣኑ የተገኘው  መረጃ  ያመለክታል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy