Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ መካከል… (ሰለሞን ሽፈራው)

0 419

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ፤ የመንግስታቸውን የ2009 በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡ እናም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ዓርብ መጋቢት 8 ቀን 2009 ዓ.ም ለዋለው የፓርላማ መድረክ የስድስት ወራት ሪፖርታቸውን ካቀረቡ በኋላ፤ በምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ ከተናገሩት አንዳንድ ነጥቦችን ማስታወስ ጠቃሚ መስሎ ተሰምቶኛል፡፡
በተለይ አንድ የተከበሩ የሕዝብ ተወካይ ምክር ቤት አባል “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክልላዊ መስተዳድሮችን በሚያዋስኗቸው አንዳንድ አካባቢዎች ተደጋግሞ የሚስተዋል ድንበር ላይ ውዝግብ እንዳለ ይታወቃል” ሲሉ ያነሱትንና የኦሮሚያን ክልል ከኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ጋር በሚዋስኑት አንዳንድ ቀበሌዎች አሁንም ድረስ እልባት ያልተገኘለት ችግር መኖሩን የጠቀሱበትን ጥያቄ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሰጡት ምላሽ ምን ይመስል እንደነበር ለማስታወስ ነው የፈለኩት፡፡
እንግዲያውስ ይህን በተጎራባች ክልላዊ መስተዳድሮች አንዳንድ አካባቢ እየተስተዋሉ ባሉት ችግሮች ዙሪያ የሚያጠነጥን ጥያቄ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ያቀረቡት የፓርላማ አባል “ቀደም ሲል የትግራይንና የአማራን ክልሎች በሚያዋስናቸው የወልቃይት ፀገዴ በተመሣሣይ ውዝግብ ተነስቶ እንደነበር የሚታወስ ነው ስለዚህ ችግሮቹን በመፍታት ረገድ መንግስት ያደረገው ጥረት ካለ ቢገልፁልን” የሚል ተጨማሪ ሃሳብ እንዳከሉ አይዘነጋም፡፡
ስለሆነም የዚህ ጥያቄ አቅራቢ የምክር ቤት አባል “ይሄን ችግር የተለያዩ የጥፋት ሀይሎች ለየራሳቸው ድብቅ አጀንዳ ማስፈፀሚያ ሊያደርጉት ሲሞክሩ ይስተዋላሉና ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩም ስለጉዳዩ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ይሰጡበት ይገባል የሚል ሃሳብ ስላለኝ ነው” ሲሉ ባጠቃለሉት ጥያቄ ላይ ተንተርሰን፤ ከአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ምላሽ መካከል ጥቂት አንኳር አንኳር ነጥቦችን እያነሳን ለማስታወስ እንሞክራለን፡፡
እናም “እኔ እንዳለኝ መረጃ ከሆነ እንደዚህ አይነቱ በአንዳንድ ክልልን ከክልል በሚያዋስኑ አካባቢዎች የሚስተዋል ውዝግብ በየትኛውም የሀገራችን ክፍል አልፎ አልፎ የሚከሰት የጋራ ችግራችን ነው ማለት የሚቻል ይመስለኛል፡፡” ያሉት ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ፤ ይህን መሠረተ ሃሣብ በምክንያታዊ ማብራሪያ አስደግፈው ያቀረቡበት አግባብ ጥያቄውን በሚያጠግብ መልኩ የመለሰ ነበር ቢባል ከእውነት መራቅ አይሆንም፡፡
በተለይም ደግሞ “ለምሣሌ ያህልም በደቡብ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ የሚገኙ የዞን እና እንዲሁም የወረዳ መስተዳድሮች በሚዋሰኑባቸው አንዳንድ ቀበሌዎች መካከል እንደዚህ አይነቶቹ ጥቃቅን አለመግባባቶች የሚስተዋሉበት አጋጣሚ እንዳለ አውቃለሁ” ሲሉ የተደመጡበት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ማብራሪያ የጉዳዩን አገር አቀፋዊ ይዘት በተሻለ የመረጃ ግብዓት አስደግፈው ግልፅ ያደረጉበት ሆኖ ነው ለእኔ የተሰማኝ፡፡
እንደርሳቸው አባባል ከሆነ ደግሞ ከላይ በተመለከተው የአንድ የምክር ቤቱ አባል ጥያቄ የተነሱትን አራት ያህል የክልል መስተዳድሮች ጨምሮ፤ ሌሎች እንደጋምቤላ አፋርና ቤንሻንጉል ጉሙዝን የመሳሰሉት ክልላዊ መስተዳድሮች ውስጥም፤ ችግሩ አልፎ አልፎ የሚስተዋልባቸው ጥቂት ተጎራባች ቀበሌዎች መኖራውን ነው አክለው ገለፁት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ፡፡ በዚህ መልኩ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ አንድንድ ጥቃቅን የተጎራባች ክልላዊ መስተዳድሮች አዋሳኝ አካባቢ ነዋሪዎች የእርስ በእርስ አለመግባባቶችን፤ በብሔርና በብሔረሰብ ሕዝቦች መካከል ያለቅራኔ መገለጫ እድርጎ መውሰድ እንደማይቻል ሲናገሩ አቶ ኃይለማርያም “ችግሩ እተስተዋለ ያለው በተጎራባች ወረዳዎች የሚገኙ ሚኒሻ ከሚኒሻ፤ ወይም ደግሞ ልዩ ፖሊስ ከልዩ ፖሊስ ጋር በሚፈጥሩት አላስፈላጊ የእርስ በእርስ ሽኩቻና ፍጥጫ ምክንያት ነው እንጂ ህዝቡ ስለዚህ ጉዳይ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም” ነበር ያሉት፡፡
የተጠቃሾቹ ሀገር አቀፍ የጋራ ችግሮቻችን ትክክለኛ መንስኤ ነው ያሉትን መሰረታዊ ጉዳይ፤ ለምክር ቤቱ ሲያብራሩም ጠቅላይ ሚኒስቴሩ “በየክልሉ የፀጥታ ስራ ለመስራት እየተባለ የሚመደበውን ዓመት በጀት ለመቀራመት እንዲያመቻቸው ሲሉ ብቻ፤ የአንዱን ብሔር ወይም ደግሞ ብሔረሰብ ህዝብ ከሌላኛው የብሔርና የብሔረሰብ ህዝብ ጋር የሚያቃቅርና የሚያጋጭ ተግባር አስከመፈፀም የሚደርሱ ቡድኖች በመንግስታችን መዋቅር ውስጥ መኖራቸውን በዚህ አጋጣሚ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ” ያሉት አቶ ኃይለማርያም የችግሩን መሪ ተዋናዮች ለመቆጣጠር የሚስችል መዋቅራዊ የተጠያቂነት መንፈስ አለመስፈኑን፤ ወይም አሰራር ትርጉም ባለው መልኩ አለመኖሩን ያልሸሸጉት ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ “ሌላው ቀርቶ የፀጥታ ማስከበር ስራ እንዲሰሩ ሲባል ጥሩ የውሎ አበል እየተከፈላቸው ወደመስክ የሚወጡና በሔዱበት ቦታ ሁሉ ምቹ የሆቴል መስተንግዶ ማግኘትን የለመዱ የመንግስት ሰራተኞችም ጭምር ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አይፈልጉም” ነው ያሉት፡፡
በእርግጥም ደግሞ ይህ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ማብራሪያ ከተጠቃሾቹ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ችግሮች ጋር በተያያዘ መልኩ መሬት ላይ የሚታየውን ተጨባጭ እውነታ ያገናዘበ ስለመሆኑ መረዳት አያዳግትም፡፡ ምክንያቱም፤ የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚን የህልውናቸው መሰረት አድርገው የወሰዱት ጥገኛ ሃይሎች፤ ከፌደራሉ መንግስት እስከ እያንዳንዱ ክልላዊ መስተዳድር ከፍተኛ የስልጣን እርከን ድረስ ዘልቀው እየገቡ ያሻቸውን ሕጋዊ አሰራርን በመተገን ቀናውን መንገድ ሁሉ ለእነርሱ ቡድናዊ ጥቅም ማስገኛነት እንዲያመች እያረጉ የሚያጣምሙበትን ሰው ሰራሽ እክል ሲፈጥሩ የሚስተዋሉበት ግልጽና ግልፅ ያልሆነ መረብ ዘርግተው እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃልና ነው፡፡
ስለዚህ፤ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ከላይ የተነሳንበትን የወቅቱን ሀገር አቀፋዊ እውነታ የሚመለከት ጥያቄ ሲመልሱ የተደመጡበት ሰፋ ያለ ማብራሪያ፤ ለኔ እንደገባኝ ከሆነ፤ የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ዓይነተኛ መገለጫ ናቸው የሚባሉት ሕጋዊ ሽፋንን እንደ ከለላ በመጠቀም የሚፈፀሙ ተግባራት የሀገራዊ ደህንነታችን ስጋት እስከመሆን የደረሱበት ሁኔታ መሆሩን የሚያመለክት ነው ማለት ይቻላል፡፡ እንጂ መሰል ችግሮችን የፌዴራላዊ ስርዓታችን የፈጠርናቸው አድርጎ መሳል ፈፅሞ ተቀባይነት እንደሌለውና ሩቅ እንደማያስኬድ እንኳንስ መንግስት አካል ጽንፈኞቹ ተቃዋሚዎችም፤ የሚጡት ጉዳይ አይሆንም፡፡ በተረፈ ግን የጠቅላይ ሚኒስቴሩ ማብራሪያ እኔ ባነሳሁት ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ አጥጋቢ መረጃ የሚያስጨብጥ ሁኖ አግኝቼዋለሁ፡፡
በበኩሌ በእገሌና በእገሌ ክልሎች ወይም በእገሌና በእገሌ ህዝቦች መካከል የድንበር ግጭት ተካሄደ እየተባለ የሚነገረው ነገርበመሰረቱችግር ያለበት ይመስለኛል። በተለያየ ምክንያት ግጭትመፈጠሩ ወይም መኖሩየሚካድባይሆንምግጭቱ የተከሰተው በድንበር ይገባኛል ጥያቄነው ብሎ ለመደምደም ወይም አውቆለማስመሰል መሞከር አንደኛው መሰረታዊ ስህተት መሆኑን ነው የማምነው።ይህ አስተሳሰብ አሁንም ድረስ ጨርሶ ካልሞተው ያለፉት ሥርዓቶች አስተሳሰብ የሚመነጭ ነው።
ሁለተኛው ስህተት ደግሞ ግጭቱ በተዋሳኝ ድንበር በሚኖሩ ሁለት ህዝቦች መካከል እንደሆነ አድርጎ መመልከቱ ነው።የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ዓይነተኛ መገለጫ የሆኑት ጠባብነትና ትምክህትበተጠናወታቸው ጥቂት ሃይሎችየሚፈፀሙ ተግባራትንየህዝቦች ፍላጎትና ተግባር አድርጎ መመልከት መሰረታዊ ስህተት ይመስለኛል፡፡ምክንያቱም በሁለት ክልሎች ውስጥየሚኖሩ ተጎራባች ህዝቦች በምንም ዓይነት ሁኔታ የግጭት ፍላጎት ሊኖራቸው እንደማይችል በተለይም በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ውስጥ የድንበር ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውስጥበአስተሳሰብም ይሁን በተግባርም አለመኖሩ ውሎ ያደረሃቅ ነው።ይህ ማለት ግን ግጭት ተፈጥሮ አያውቅም ወይም ወደፊትም አይኖርም ማለቴ አይደለም። ከድንበር ማዶ የሚኖሩ ህዝቦች በተለያየ ጊዜ በውሃም በግጦሽ መሬትም አልፎ አልፎ ሲጋጩ የነበሩባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ።ይህ ችግር ደግሞ በመሰረቱከድህነታችን ጋር የተያያዘ ነው። ከድህነት በፍጥነት መላቀቅለአገራችን ህልውና ቀጣይነት ብቸኛው መፍትሄ መሆኑን ከሚያሳዩን እውነታዎችም አንዱ ይህን መሰሉ ግጭት እንደሆነ ይታወቃል። ያም ሆኖ ግንተዋሳኝ ህዝቦች በክፉም በደጉም ለዘመናት አብረው የኖሩና ወደፊትም አብረው የሚኖሩህዝቦች መሆናቸውን ዘንግቶ ህዝብን ለህዝብ ለማጫረስ ያለውንም የሌለውን እየፈጠሩ ማራገብፍጹም ሃላፊነት የጎደለው፣ ለህዝቦቹም ሆነ ለመላው አገራችን ህዝቦች የማይጠቅም ወንጀል መሆኑ መታወቅ አለበት።
አንድ የጋራ ማህበረሰብ በመፍጠር ላይ ያለመው የፌዴራሊዝም ሥርዓታችንም ትኩረቱን በድንበር ጉዳይ ላይ ሳይሆን በህዝቦች የጋራ ልማትና ተጠቃሚነት ላይ ማድረጉእዚያው በድንበርህ፣ እኔም በድንበሬ የሚለውን የቆዬ አስተሳሰብ ከሥሩ እንደናደውሌላው ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ ነው።በህዝቦች መካከል ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ይህን መሰሉ አስተሳሰብ እየሞተ እንደመጣው ሁሉየጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ሥርዓተ ቀብሩ መፈጸሙ አይቀሬ ነው። ለዚህም ይመስላልጥቂት ኪራይ ሰብሳቢዎች ከዚህ ወዲህ የኔ፣ ከዚያ ወዲያ የአንተ በሚል በድንበር ላይ የተንጠለጠለ ልዩነት እያራገቡበጠባብነትና በትምክህት አስተሳሰብ ህዝብን እየነዱ የእነሱ ጥገኛ አስተሳሰብ መጠቀሚያ ለማድረግ ባለ በሌለ አቅማቸው እየተፍጨረጨሩ ያሉት።
በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ቦታ የሌለውን አስተሳሰብ ነፍስ ዘርተውበት ህዝብን ከህዝብ ለማጫረስ እየተፍጨረጨሩ ያሉትን ኪራይ ሰብሳቢዎች መንግሥት ለፍርድ እንደሚያቀርባቸው ጥርጥር የለኝም። ያረጀ ያፈጀውን የዱሮ ሥርዓቶች አስተሳሰብ በመታገል በኩል ግን አሁንምቀደም ሚና መጫዎት ያለበት ብዙሃኑ ህዝባችን በመሆኑ እያንዳንዱ ዜጋ ለጥቂቶች መጠቀሚያ ከመሆን ራሱን በማቀብ፣ ዋነኛ ተዋናዮችንም ለህግ አሳልፎ በመስጠት የዜግነት ድርሻውን ሊወጣ ይገባዋል ባይ ነኝ።መዓሰላማት!

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy