Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኬንያ 31 የአልሸባብ ታጣቂዎች መግደሏን አስታወቀች

0 538

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኬንያ ወታደሮች 31 የአልሸባብ ታጣቂዎችን በደቡብ ሶማሊያ አካባቢ ባዳዴ በሚባል ቦታ በተደረገ ውጊያ እንደገደለች አስታውቃለች፡፡

የኬንያ መንግስት ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሞቱት የአልሸባንብ ታጣቂዎች በተጨማሪ 11 AK-47 ጠመንጃዎች፣ 4 በቤት ውስጥ የተሰሩ ፈንጂዎች፣ የመገናኛ መመሳሪያዎች፣ ምግብና ወታደራዊ የደንብ ልብሶች መማረካቸውን ገልፀዋል፡፡

እሁድ ቀን በአልሸባብ ላይ በተወሰደው እርምጃ የኬንያ ምድር ጦር በሄሊኮብተር የተደገፈ ጥቃት እንደሰነዘረ መግለጫው ያመለክታል፡፡

ኬንያ ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ የላከችው እ.ኤ.አ ጥቅምት 2011 ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሚደገፈው የአሜሶም ጦር ስር በመታቀፍ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy