Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ወበቃማው የበልግ አየር ሁኔታ በቀጣይ ወራትም እንደሚቀጥል የብሄራዊ ሜቴዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ

0 422

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኢትዮጵያ በበልግ ወራት የሚከሰተው ወበቃማ የአየር ሁኔታ እስከ ግንቦት ድረስ ሊቀጥል እንደሚችል በብሄራዊ ሜቴዎሮሎጂ ኤጀንሲ የሜቴዎሮሎጂ ባለሞያ አቶ ዳዲሞስ ወንድይፍራው ለኢቢሲ ገልፀዋል፡፡

ከየካቲት ጀምሮ እስከ ግንቦት በሚዘልቀው የበልግ ወቅት ዝናብ ሰጪ የአየር ክስተቶች የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው መረጃዎች ስለሚጠቁሙ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉም አቶ ዳዲሞስ ገልፀዋል፡፡

በበልግ ወራት በየመሀከሉ የሚጥለው ዝናብ ምቾት የሚነሳውን ወበቃማ የአየር ሁኔታ እንደሚያረግበውም ነው ባለሞያው የገለፁት፡፡

በአገሪቱ ቆላማ ስፍራዎች የሙቀት መጠን ከ40 ዲግሪ ሴሊሸስ በላይ መመዝገቡን የገለፁት ባለሞያው ሰሞኑን በአዲስ አበባና አካባቢዋ የየቀኑ ከፍተኛ የአየር ሙቀት በአማካኝ ከ25.6 ዲግሪ ሴሊሸስ እስከ 27.8 ዲግሪ ሴሊሸስ መመዝገቡን አስታውቀዋል፡፡

በበልግ ወቅት የሚፈጠረው የደመና ሽፋን ዝናብ የመስጠት አቅም ሳይኖረው ሲቀር በአየር ውስጥ እርጥበት እንዲጨምር ያደርጋል፤ ይህም ምቾት የሚነሳ ወበቃማ የአየር ሁኔታ እንደሚፈጥር ባለሞያዎች ይተነትናሉ፡፡

ሪፖርተር፡- ናትናኤል ፀጋዬ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy