Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ድርጅት ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ ይካሄዳል

0 347

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ላይ የሚመክረው አራተኛው ዓለም አቀፉ የአቪዬሽን ድርጅት ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።በአፍሪካ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ሲምፖዚየም ከሚያዚያ 3 እስከ 6 ቀን 2009 ዓ.ም  ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንዳሉት ሲምፖዚየሙ በዘርፉ የሚሰሩ ባለሙያዎች እርስ በእርሳቸው እንዲቀራረቡ የማድረግ ሚና ይጫወታል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ያሉ ዘመናዊ መሣሪያዎችና ስልቶች እንዲተዋወቁ እንዲሁም ለዘርፉ የተሻለ አማራጭ ለማፈላለግ ዕድል እንደሚፈጥርም ገልጸዋል።ይህም በዘርፉ ያለውን የካበተ ልምድ እርስ በእርስ በመለዋወጥ ዘርፉን ለማዘመን እንደሚረዳ ነው የጠቆሙት።

ሲምፖዚየሙ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ መካሄዱ፤ የአህጉሪቱ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ትኩረት እንዲያገኝና ሊያድግ በሚችልበት ጉዳይ ላይ ምክክር ለማድረግ እንደሚጠቅም አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድን በሲምፖዚየሙ ይበልጥ ለማስተዋወቅ፤ በተለይም የአቪዬሽን አካዳሚውን ለማጠናከር ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል። ሲምፖዚየሙ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ አየር መንገድና በመንግሥታቱ ድርጅት የአቪዬሽን ድርጅት ትብብር ነው።በሲምፖዚየሙ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ500 በላይ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ የተሰማሩ ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።ሲምፖዚየሙ “በጋራ አቅምን ለመገንባት ሥልጠና እንጨምራለን” በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy