Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የህወሀት ማዕከላዊ ኮሚቴ የጥልቅ ተሃድሶ አፈፃፀምን ገመገመ

0 341

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በትግራይ ክልል የተካሄደው የጥልቅ ተሀድሶ በቀጣይ ለሚካሄዱ የልማት ስራዎች እና መልካም አስተዳድርን የማስፈን እንቅስቃሴዎች ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን የህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ አስታወቀ።

የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ከመጋቢት 15 እስከ 17 2009 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ሲያካሂድ የነበረውን መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት አጠናቅል።

በስብሰባውም በክልሉ ሲካሄድ የነበረው የጥልቅ ተሀድሶ አፈፃፀም እና ባለፉት 6 ወራት በክልሉ የተሰሩ ስራዎችን ገምግሟል።በጥልቅ ተሃድሶ ግምገማው ከከፍተኛ አመራር እስከ ድርጅት አባል እንዲሁም ሲቪል ሰርቫንቱ እና ህዝቡ በጥልቀት ግምገማ ማድረጉን መእከላዊ ኮሚቴው አስታውቋል።

ይህም ለቀጣይ ትግል ምቹ ሁኔታን የፈጠረ መሆኑን የህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ ከስብሰባው በኋላ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።ይህንን በተግባር ለማረጋገጥም ህዝቡ በግምገማው ያደረገውን አስተዋጽኦ በተግባርም አጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ እንደሚሰራ ድርጅቱ አስታውቋል።

የልማት ስራዎችን በተመለከተም በገጠር በተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ በመስኖ፣ በትምህርት እና በጤና አበረታች ውጤት መመዝገቡን ማእከላዊ ኮሚቴው አስታውቋል።

በከተማም በጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት፣ በሲቪል ሰርቫንቱ እና በትምህርት ከጥልቅ ተሃድሶው ጎን ለጎን ጥሩ የሚባል ውጤት መመዝገቡን ማእከላዊ ኮሚቴው ተመልክቷል።በቀጣይም በጥልቀት መታደሱን በማስቀጠል እና የድርጅቱን መዋቅር በማጠናከር ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በህብረት በመስራት ትምክህትና ጠባብነትን እንደሚታገል ማእከላዊ ኮሚቴው አስታውቋል።

 

በሙሉጌታ አጽበሃ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy