Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የማንጠቀምበትን ህግ ከምናወጣ፤ የምንጠቀምበትን አዕምሮ እናዳምጥ!

0 992

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኒቨርሲቲ የሚያስተምሩ ፕሮፌሰር ጓደኛሞች ናቸው፡፡ የእረፍት ጊዜያቸውን ሁካታውና ጫጫታው ከበዛበት ከተማ ገለል ብለው ማሳለፍ ፈለጉና ወደ ገጠር ሄዱ፡፡ በማለዳ ተነስተው ወደ አንድ አርሶአደር መንደር ደርሰው የናፈቁትን ንጹህ አየር፣ ልምላሜ የተሞላበትን ጋራ ሸንተረር እየተዘዋወሩ በመመልከት መንፈሳቸውን አስደሰቱ። ነፋሻውን አየር እየተመገቡም ሲደሰቱ ዋሉ፡፡

ምሽት ላይ ፕሮፌሰሮቹ በገጠር ያሉትና ያልተማሩት አርሶአደሮች ስራቸውን የሚሰሩት ደንብና ስርዓት ባለው ሁኔታ መሆኑን ሲያስተውሉ በጣም ተደነቁ፡፡ ማሳቸውን በአንድ በኩል ጥራጥሬ በሌላ በኩል ስንዴውን፣ጤፉን፣ ገብሱን.. በተረፈው መሬት ደግሞ ጣፋጭ የሆኑ አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን ተክለዋል። ጤንነታቸው የተጠበቀ ከብቶች በተዘጋጀላቸው የግጦሽ ስፍራ ተሰማርተዋል፡፡

ፕሮፌሰሮቹ ባዩት ነገር እጅግ ተደንቀው «እንዴት እነዚህ ያልተማሩ አርሶአደሮች እርሻቸውን እንዲህ በሚገባ አደራጅተው ሊመሩ ቻሉእያሉ እርስ በርሳቸው ከተነጋገሩ በኋላ አንዱን አርሶአደር ጠርተው ጠየቁት፡፡ አርሶእደሩም እንዲህ በማለት መለሰላቸው፡፡«እንደምታውቁት እኔ ያልተማርኩ የተፈጥሮ እውቀቴን ብቻ ነው ጥቅም ላይ የማውለው» አላቸው፡፡ ሰው በተፈጥሮው አዋቂ እንደሆነ አይካድም ያንን እውቀቱን ለማበልፀግ ደግሞ መደበኛ ትምህርት ያስፈልገዋል። በመደበኛ ትምህርት ደግሞ አድርግ፣ አታድርግን ጨምሮ ሌሎች ህግጋትና መመሪያዎችን እንዲረዳ ይደረጋል። እነዚህ አርሶ አደሮች ተፈጥሮ በለገሰቻቸው እወቀት ተጠቅመው እራሳቸውን፣እንስሶቻቸውንና አካባቢያቸውን በሚገባ በመጠበቃቸው ተመራመርን ፣ አወቅን የሚሉትን ሳይቀር ያስደምሟቸዋል።

ህግና መመሪያ የሚወጣው የሰው ልጆች በተፈጥሮ ያገኙትን፤ አንዲሁም በትምህርት ያበለፀጉትን እውቀቶች አንዲያዳብሩበት ያገለግላቸዋል ተብሎ ይታሰባል። ለዚህም ነው በተለያዩ መንገዶች በተፈጥሮ እውቀት ስንመራቸው የነበሩ እውነቶችን በህግና በመመሪያ የምናስራቸው። በየትኛውም ዓለም ህግና መመሪያዎች፤ አዋጆችና ደንቦች ከመውጣታቸው በፊት ሁሉም በተሰማራበት የስራ መስክ የተፈጥሮ እውቀቱን ይጠቀም አንደነበር አይካድም። በሂደት ግን በተፈጥሮ የተገኘን እውቀት በህግና በመመሪያዎች እንዲበለፅግ የተደረገው። ህግና መመሪያዎችን የተላለፉትንም ለመቅጣት እንዲያስችል የፍታብሄርና የወንጀል ህጎችን ተግባራዊ ተደርገዋል። በአንፃሩ ደግሞ በርካታ የሚባሉ ህጎችና መመሪያዎች ቢወጡም ተግባራዊ ባለመደረጋቸው የቅሬታ መንጮች ሲሆኑ ተስተውሏል።ዝግጅት ክፍላችንም በተደጋጋሚ «ህጎችና መመሪያዎች ተግባራዊ ይሁኑ» በማለት አቋሙን ሲያንፀባርቅ ቆይቷል። ዛሬም አዋጁ ተግባራዊ ይሁን እያለ ይጮሃል።

በየካቲት ወር 1999 በወጣው አዋጅ ቁጥር 513/1999 «የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ አዋጅ» አንቀጽ ስምንት ንዑስ አንቀጽ አንድ እስከ ሶስት ላይ የፕላስቲክ ከረጢቶችን በተመለከተ እንዲህ ይላል «በስብሶ ወደ አፈር የሚደባለቅ መሆን አለመሆኑን የሚያሳይ ምልክት ያልተደረገበትን የፕላስቲክ ከረጢት ለገበያ ማቅረብ የተከለከለ ነው። ይህ ማለት ውፍረቱ 0 ነጥብ 03 ሚሊ ሜትር እና ከ0ነጥብ03 ሚሊ ሜትር በታችም ሆኖ በስብሶ ከአፈር ጋር የማይዋሃድ የፕላስቲክ ከረጢት የማምረት ወይም ወደ አገር ውስጥ የማስገባት ፈቃድ መስጠት የተከለከለ ነው»

አዋጁ ይህን ቢልም ከደረጃ በታች የሚያመርቱ የፕላስቲክ ከረጢት ፋብሪካዎች መኖራቸው እየታወቀ እርምጃ ለመውሰድ ወይም አዋጁን ተፈፃሚ ማድርግ አልተቻለም።

አሁን ባለው መረጃ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 400 የፕላስቲክ ፋብሪካዎች ይገኛሉ። በድሬዳዋና በአዲስአበባ በተደረገ ጥናት 24ቱ በህገወጥ መንገድ አንደሚሰሩ ተረጋግጧል። በተጨማሪም በአገሪቱ በ24 ከተሞች ላይ በተሰራው ጥናት ደግሞ በዓመቱ ከሚሰበሰበው ቆሻሻ ወስጥ ከ5 እስከ 9 በመቶ የሚሆነው የፕላስቲክ ቆሻሻ ነው። ይህም አደገኛነቱን የከፋ የሚያደርገው ተመልሶ ጥቅም ላይ የማይውል በመሆኑ ነው።

የፕላስቲክ ከረጢቶች በቀላሉ መበስበስ ስለማይችሉ በአርሻ ምርት ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖ ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል። በእንስሳት ጤናና የአመጋገብ ስርዓት ላይ ጉዳት እንደሚያስከትሉም በጥናት ተረጋግጧል፡፡ የፕላስቲክ ከረጢቶቹ ሲቃጠሉ የሚያመነጩት በካይ ጋዝ በአካባቢና በሰዎች የመተንፈሻ አካላት ጤንነት ላይ የሚያደርስው ጉዳትም ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል።

የፕላስቲክ ምርቶች በየቦታው ሲቃጠሉ «ሚቴን» የተባለ በካይ ጋዝ ስለሚያመነጩ በጤናና በአካባቢ ላይ ጉዳት ያደርሳሉ። በዓለም ላይ የፕላስቲክ ውጤቶች 70 በመቶው ወደ ቆሻሻነት በመለወጥ ብክለትን ያስከትላሉ።ውሃ በማቆር ፈሳሽና አየር ወደ አፈር እንዳይገባ ይገድባሉ። በአዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች ያለ አግባብ በሚወገዱ የፕላስቲክ ውጤቶች የውሃ መውረጃ ቦዮች እየተደፈኑ ጎርፍ በመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት እንዲያስከትል ያደርጋል።

ለአየር ንብረት የማይጋለጥ አረንጓዴ ኢኮኖሚ መገንባት የሕልውና ጉዳይ ነው። በመሆኑም የፕላስቲክ ከረጢት በአዋጁ መሰረት እንዲስተናገድ ሁሉም ያገባዋልና እስተዋጽኦ የማድረግ ግዴታ አለበት። በተለይ ካለ ፈቃድ የተከለከለ የፕላስቲክ ከረጢት በሚያመርቱት ላይ ፈጣን የእርምት እርምጃ ሊወሰድ ይገባል። በሕጋዊ ፈቃድ ወደ ምርት የሚገቡና ወደፊትም በመስኩ ለሚሰማሩ አምራቾች የተቀናጀ የቁጥጥርና የክትትል ስርዓት መዘርጋት አለበት።

ዛሬ ተፈጥሮ በለገሰቻቸው አውቀት ለአካባቢያቸው የሚቆረቆሩና የሚንከባከቡ አርሶአደሮች ሳይንስ ባመጣባቸው ጦስ እየተጎዱ ነው። በመሆኑም የማንጠቀምበትን ህግ ከምናወጣ፤ የምንጠቀምበትን አዕምሮ ማስቅደም አንዳለብን ልንረዳ ይገባል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy