Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ጀመረ

0 339

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ የግማሽ ዓመት መደበኛ  ስብሰባውን በባህር ዳር ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

መደበኛ ስብሰባው ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ የተከናወኑ ስራዎችና የጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄው ያለበት ደረጃ ይገመገማሉ።

ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና ሌሎችንም ችግሮች ከመፍታት አኳያ የተከናወኑ ስራዎች ላይ ኮሚቴው በትኩረት እንደሚወያይባቸው ነው የተነገረው።

በገጠር የህብረተሰቡን ምርታማነት ለማሳደግ የተሰሩ ስራዎች፣ በከተማ የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት እና የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፎች እንዲሁም የመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስቲሪዎች በተለይም የኢንዱስትሪ ፓርክ አፈፃፀሞች በዝርዝር እንደሚገመገሙ ተጠቁሟል።

ድርጅቱ እቅዶችን በስኬት ለመፈፀምና የመሪነቱን ሚና ለመወጣት የሚያግዙ የትኩረት ነጥቦችን እንደሚያስቀምጥም ተገልጿል።

በስብሰባው ላይ የቀድሞ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና የሜትሮፖሊታንት ከተማ ከንቲባዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ከማዕከላዊ ኮሚቴው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ዛሬን ጨምሮ ለአራት ቀናት ይካሄዳል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy