Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የተካሄደው የጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄ የአስተሳሰብ አንድነትን ያመጣ ነው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ

0 1,056

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የተካሄደው የጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄ የአመራሩን የአስተሳሰብ አንድነትና ግልጽነት ያመጣ  መሆኑን የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለምነው መኮንን ገለጹ።ማዕከላዊ ኮሚቴው በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ በተባለው አካባቢ በደረሰው አደጋ የሰው ህይወት በመጥፋቱ የተሰማውን ሃዘን ገልጿል።

ላለፉት አራት ቀናት ሲካሔድ የቆየውን የማዕከላዊ ኮሚቴ ጉባኤ መጠናቀቅ አስመልክቶ ኃላፊው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት የጉባኤው ትኩረት የተሃድሶ ንቅናቄው ያስገኘውን ውጤት ማዕከል ያደረገ ነው።

ያለፉት 15 ዓመታት ስኬቶችን በመዘከር በሂደቱ የተፈጠሩ የአስተሳሰብና የተግባር ዝንፍቶችን ለማስተካከል ወደ ተሃድሶ ንቅናቄ መገባቱን ገልጸው በዚህም ችግሮችን በመለየት አስፈላጊው የማስተካከያ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል።

በተሃድሶውም ከክልሉ ካቢኔ 50 በመቶ፣ ከዞን 43 በመቶ፣ ከወረዳ 47 በመቶና ከቀበሌ ደግሞ 28 ነጥብ ሰባት በመቶ የሚሆነው የአመራር ቦታ ውጤታማነትን፣ አግባብነትንና እውቀትን መሰረት አድርጎ በአዲስ መደራጀቱን ገልጸዋል።በሁለት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ላይም የእገዳና የከባድ ማስጠንቀቂያ ውሳኔ ማዕከላዊ ኮሚቴው አሳልፏል።ከ5ሺህ 300 በላይ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና  የቀበሌ አመራሮች ላይ ከሃላፊነት ከማንሳት እስከ ከባድ ማስጠንቀቂያ የሚደርስ እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል፡፡

ህዘባዊ አንድነትንና ትስስርን የሚጎዱ የትምክህትና የጠባብ አስተሳሰቦችንና ጸረ ዴሞክራሲያዊ አካሔዶችን በመታገል የክልሉን ሰላምና ልማት ማፋጠን እንደሚገባ ማዕከላዊ ኮሚቴው ማስገንዘቡን አስረድተዋል።

በግብርና ምርታማነት ባለፈው መኸር የተገኘውን የምርት እድገት በቀጣይም አጠናክሮ ለማስቀጠል ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ርብርብ እንዲደረግ አቅጣጫ መቀመጡን ገልጸዋል።

የተለዩ ስራ አጥ ወጣቶችን ወደ ስራ በማስገባት በኩል መንግስት የመስሪያ ቦታና ብድር በማቅረብ፣ ስልጠና በመስጠትና በሌሎች ድጋፎች የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መግባባት ላይ ተደርሷል።

ህብረተሰቡ ያነሳቸውን ችግሮች በዴሞክራሲያዊ አግባብ ለመፍታት ብዙ ርቀት መጓዙን ጠቁመው “በቀጣይ ህዝቡን በማሳተፍ ተግባራዊ ርብርብ እንዲደረግ አቅጣጫ ተቀምጧል” ብለዋል።

በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ እየተባለ በሚጠራው አካበቢ ለደረሰው የሞት አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን በመግለጽ ለተጎጂ ቤተሰቦችም በማዕከላዊ ኮሚቴው ስም መጽናናትን ተመኝተዋል።

ለተከታታይ አራት ቀናት በተካሄደው የማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ላይም 22 የቀድሞ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና ዘጠኝ የዞንና የትላልቅ ከተሞች አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎችን በማሳተፍ በአቅጣጫዎቹ ላይ የጋራ መግባባት መወሰዱ ተመልክቷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy