Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአለም ባንክ ለአፍሪካ የ57 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ

0 658

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአለም ባንክ ለአፍሪካ የ57 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን አስታወቀ።ባንኩ በቀጣዮቹ ሶስት አመታት ነው ከስሀራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ለሚያካሂዱት የልማት ስራዎች ድጋፉን የሚያደርገው።

ከአጠቃላይ ድጋፉ 45 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላሩ ከአለም አቀፉ የልማት ማህበርና የአለም ባንክ ፈንድ ለአለም ድሃ አገራት ከሚሰጠው እርዳታና ከወለድ ነፃ ብድር የሚገኝ ነው።የባንኩ ፐሬዝዳንት ጂም ዮንግ ኪም እንደገለፁት፥ ለግሉ ዘርፍ የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲውል ደግሞ 8 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ተመድቧል።

ከዚህም በተጨማሪ መካከለኛ የምጣኔ ሀብት እድገት ላስመዘገቡ የአህጉሪቱ ሀገራት ባንኩ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው ፕሬዚዳንቱ የጠቆሙት።ባንኩ ያደረገው ድጋፍ በአህጉሪቱ የትምህርት፣ ጤና፣ ንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን እና ግብርና ዘርፎችን ለመደገፍ ይውላል ተብሏል።

በአለም አቀፉ የልማት ማህበር በኩል የሚደረገው ድጋፍ ከሰሃራ በታች በሚገኙ ሀገራት ከዚህ ቀደም የተጀመሩ 448 ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እንደሚውል ተገልጿል።

የቡድን 20 አባል አገራት ባለፈው አርብና ቅዳሜ በጀርመን ባካሄዱት ስብሰባ ከአፍሪካ ጋር በቅርበት ለመስራት እና ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸው ይታወሳል። ምንጭ፦ http://africa.cgtn.com/

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy